+ -

عَنْ سَعْدٍ رضي الله عنها قَالَ:
جَاءَ أَعْرَابِيٌّ إِلَى رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: عَلِّمْنِي كَلَامًا أَقُولُهُ، قَالَ: «قُلْ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، اللهُ أَكْبَرُ كَبِيرًا، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ كَثِيرًا، سُبْحَانَ اللهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ، لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللهِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ» قَالَ: فَهَؤُلَاءِ لِرَبِّي، فَمَا لِي؟ قَالَ: «قُلْ: اللهُمَّ اغْفِرْ لِي وَارْحَمْنِي وَاهْدِنِي وَارْزُقْنِي».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2696]
المزيــد ...

ከሰዕድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"አንድ የገጠር ሰው ወደ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመምጣት እንዲህ አለ: 'የምለውን ቃላት አስተምሩኝ?' እርሳቸውም 'ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ፤ አሏሁ አክበር ከቢራ፣ ወልሐምዱሊላሂ ከሢራ፣ ወሱብሓነሏሂ ረቢል ዓለሚን፣ ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐዚዚል ሐኪም በል።' አሉት። (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። አላህ እጅግ ታላቅ ነው፤ ለአላህ ብዙ ምስጋና የተገባው ነው፤ የዓለማቱ ጌታ አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ በቀር ሀይልም ብልሀትም የለም።) እርሱም 'እነዚህ ቃላት ጌታዬን (የማወድስበት) ናቸው። ለኔስ (የምለምንበት)?' አላቸው። እርሳቸውም 'አላሁመጝፊር ሊ ወርሐምኒ ወህዲኒ ወርዙቅኒ። በል!' አሉት።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ማረኝ፣ እዘንልኝ፣ ምራኝ፣ ሲሳይን ለግሰኝ።)

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2696]

ትንታኔ

አንድ የገጠር ነዋሪ የሆነ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሚናገረውን ውዳሴ እንዲያስተምሩት ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ እንዲህ አሉት: "እንዲህ በል! "ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ" በተውሒድ የምስክር ቃል ጀመሩ። (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ብቸኛና አጋር የሌለው ነው።) "አሏሁ አክበር ከቢራ" ማለትም "አላህ ከሁሉም ነገር የበለጠ እጅግ ታላቅ ነው።" ማለት ነው። "ወልሐምዱ ሊላሂ ከሢራ" ማለትም "ለአላህ በባህሪዎቹ፣ በድርጊቶቹ፣ በማይቆጠሩ ፀጋዎቹ ብዙ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው። "ሱብሐነሏሂ ረቢል ዓለሚን" ማለትም "አላህ ከጉድለት የጠራ የፀዳ ነው።" ማለት ነው። "ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐዚዚል ሐኪም" ማለትም "በአላህ እገዛና መግጠም ካልሆነ በቀር ከአንድ ሁኔታ ወደ ሌላ ሁኔታ መለወጥ የለም።" ማለት ነው። ሰውዬውም "እነዚህ ቃላት ጌታዬን ለማውሳትና ለማላቅ ነው። ለነፍሴ የማደርገው ዱዐስ?" ብሎ ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "እንዲህ በል!" አሉት። "አልላሁመጝፊርሊ" (አላህ ሆይ! ማረኝ) ወንጀሎችን በመማርና በመሸሸግ "ወርሐምኒ" (እዘንልኝ) ሃይማኖታዊና ዱንያዊ ጥቅሞችን ለኔ በማድረስ እዘንልኝ። "ወህዲኒ" (ምራኝ!) ወደ ተሻለ ሁኔታና ቀጥተኛውን መንገድ ምራኝ። "ወርዙቅኒ" (ሲሳይን ለግሰኝ!) ሐላል ገንዘብን፣ ጤናን፣ ሁሉንም መልካምና ደህንነት ለግሰኝ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህን በ"ተህሊል"፣ በ"ተክቢር"፣ በ"ተሕሚድ"ና በ"ተስቢሕ" በማውሳት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ከዱዓእ በፊት አላህን ማውሳትና ማወደስ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  3. የሰው ልጅ በምርጥ ዱዓ፣ በቁርአንና በሐዲሥ በመጡ ዱንያዊና አኺራዊ መልካም ነገሮችን የሰበሰቡ በሆኑ ዱዓዎች ማድረጉ እንደሚወደድ እንረዳለን። በፈለገው ዱዓ ማድረግም ይችላል።
  4. አንድ ባሪያ ለዱንያውና አኺራው የሚጠቅመውን ነገር በመማር ላይ መጓጓት ይገባዋል።
  5. ምህረትን፣ እዝነትንና ሲሳይን በመፈለግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። እነዚህ ጉዳዮችም የመልካም ነገሮች መሰብሰቢያ ናቸው።
  6. ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡመታቸው የሚጠቅማቸውን ነገር በማስተማር ላይ መራራታቸውን እንረዳለን።
  7. ከምህረት መለመን በኋላ እዝነትን መለመን የተወሳው ንፅህናው እንዲሟላ ነው። ምህረት ማለት ወንጀልህ መሸሸጉ፣ መታበሱና ከእሳት መዳን ሲሆን እዝነት ደግሞ መልካምን ማግኘትና ጀነት መግባት ነው። ትልቁ ስኬት ይህ ነው።