عَنْ أَبِي أُمَامَةَ البَاهِلِيِّ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: ذُكِرَ لِرَسُولِ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَجُلاَنِ أَحَدُهُمَا عَابِدٌ وَالآخَرُ عَالِمٌ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«فَضْلُ العَالِمِ عَلَى العَابِدِ كَفَضْلِي عَلَى أَدْنَاكُمْ»، ثُمَّ قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «إِنَّ اللَّهَ وَمَلاَئِكَتَهُ وَأَهْلَ السَّمَوَاتِ وَالأَرَضِينَ حَتَّى النَّمْلَةَ فِي جُحْرِهَا وَحَتَّى الحُوتَ لَيُصَلُّونَ عَلَى مُعَلِّمِ النَّاسِ الخَيْرَ».
[حسن لغيره] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 2685]
المزيــد ...
አቡ ኡማመተል ባሂሊይ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «ለአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለሁለት ሰዎች ተነገራቸው። አንደኛው አላህን አብዝቶ የሚገዛ ሲሆን ሌላኛው ዓሊም (አዋቂ) ነው። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ:
"አዋቂ (ዐሊም) አላህን አብዝቶ ከሚገዛ ባሪያ (ከዐቢድ) ጋር ያለው ልዩነት እኔ ከናንተ መካከል ከዝቅተኛው ሰው ጋር እንዳለኝ ልዩነት ነው።" ቀጥለው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ "አላህ፣ መልአክቶቹና፣ ጓድጓዷ ውስጥ ያለች ጉንዳን፣ ዓሳ እንኳን ሳትቀር የሰማያትና የምድር ነዋሪዎች መልካም በሚያስተምሩ ላይ ሶላት ያወርዳሉ።"»
[Hasan/Sound by virtue of corroborating evidence] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2685]
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ሁለት ሰዎች ተወሱ። አንዱ ዓቢድ (አላህን አብዝቶ የሚገዛ) ሲሆን ሌላኛው ዐሊም (አዋቂ) ነው። ማንኛቸው ይበልጣል ተብለው ተጠየቁ።
ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡ "የሸሪዓን እውቀቶች አውቆ በእውቀቱ ከመስራት አልፎ የሚያስተምር ሰው ማወቅ ያለበትን ግዴታዎች አውቆ ራሱን ለአምልኮ ብቻ ነፃ ካደረገ ሰው ጋር ያለው ልዩነት ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሶሓቦች ሁሉ ዝቅተኛ ከሆነው ጋር እንዳላቸው ልዩነትና ደረጃ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የዚህን ምክንያት እንዲህ በማለት ገለፁ። አላህ ሱብሓነሁ፣ የዐርሽ ተሸካሚ የሆኑ መልአክቶቹ፣ የተቀሩትም ሰማይ ውስጥ የሚኖሩ መልአክቶች፣ በምድር የሚኖሩ ሰዉም ጂንም አጠቃላይ እንስሶችም፣ ጉንዳን እንኳን ከምድር በታች ባለው ቤቷ ሳይቀር፣ አሳና የባህር እንስሶችም ሳይቀሩ የየብሱም ይሁን የባህሩ እንስሶች ባጠቃላይ እነዚህ ሁሉ መዳኛቸውና መድህናቸው የሆነውን መልካም ነገርና ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ለሚያስተምር ሰው ዱዓ ያደርጋሉ።