عَنْ أَبَانَ بْنِ عُثْمَانَ قَالَ: سَمِعْتُ عُثْمَانَ ابْنِ عَفَّانَ رضي الله عنه يَقُولُ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«مَنْ قَالَ بِسْمِ اللَّهِ الَّذِي لَا يَضُرُّ مَعَ اسْمِهِ شَيْءٌ، فِي الْأَرْضِ، وَلَا فِي السَّمَاءِ، وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ، ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، لَمْ تُصِبْهُ فَجْأَةُ بَلَاءٍ، حَتَّى يُصْبِحَ، وَمَنْ قَالَهَا حِينَ يُصْبِحُ ثَلَاثُ مَرَّاتٍ، لَمْ تُصِبْهُ فَجْأَةُ بَلَاءٍ حَتَّى يُمْسِيَ»، قَالَ: فَأَصَابَ أَبَانَ بْنَ عُثْمَانَ الْفَالِجُ، فَجَعَلَ الرَّجُلُ الَّذِي سَمِعَ مِنْهُ الْحَدِيثَ يَنْظُرُ إِلَيْهِ، فَقَالَ لَهُ: مَا لَكَ تَنْظُرُ إِلَيَّ؟ فَوَاللَّهِ مَا كَذَبْتُ عَلَى عُثْمَانَ، وَلَا كَذَبَ عُثْمَانُ عَلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَلَكِنَّ الْيَوْمَ الَّذِي أَصَابَنِي فِيهِ مَا أَصَابَنِي غَضِبْتُ فَنَسِيتُ أَنْ أَقُولَهَا.
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه والنسائي في الكبرى وأحمد] - [سنن أبي داود: 5088]
المزيــد ...
ከአባን ቢን ዑሥማን እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑሥማን ቢን ዐፋን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው: "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው:
‹ሶስት ጊዜ 'ቢስሚላሂለዚ ላየዱሩ መዐስሚሂ ሸይኡን ፊልአርዲ ወላፊስሰማእ ወሁወስ'ሰሚዑል ዐሊም' (ትርጉሙም: በዚያ ከስሙ ጋር በምድርም ይሁን በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳ በሆነው እንዲሁም ሰሚና አዋቂ በሆነው አላህ ስም።) ያለ ሰው እስኪነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ጊዜም ሶስት ጊዜ ያላት ሰው እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም።› አባን ቢን ዑሥማንን የግማሽ አካል ሽባነት አገኘውና ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም አተኩሮ ተመለከተው። አባንም ለርሱ እንዲህ አለው: እንደዚ አተኩረህ የምታየኝ ምን ሆነው ነህ? በአላህ እምላለሁ! በዑሥማን ላይ ምንም አልዋሸሁም! ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ምንም አልዋሸም። ነገር ግን ዛሬ የደረሰብኝ ነገር የደረሰው ተቆጥቼ ስለነበር ይህን ዚክር ማለት ረስቼ ስለነበር ነው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 5088]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁሉ ቀን ጎህ ከቀደደ በኋላ ንጋት ላይና ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ደግሞ ሁሌ ምሽት ላይ ሶስት ጊዜ ይህንን ዚክር ያለ ሰው:(ቢስሚላሂ) በአላህ ስም ከሁሉም ጎጂ ነገር እጠበቃለሁም እታገዛለሁም። (ያ ስሙን ከማውሳት ጋር) ምንም ያህል ቢተልቅ (አንዳችም የማይጎዳው) (በምድርም ውስጥ) ከምድር የሚወጡ በሆኑ መከራዎችም (በሰማይ ውስጥም) ከሰማይ የሚወርዱ በሆኑ መከራዎችም (እርሱ ንግግራችንን ሰሚ) ሁኔታችንንም (አዋቂ ነው።) የምንጎዳ አይደለንም።
: በሚያመሽ ወቅት የተናገራት እስኪያነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ወቅት የተናገራት ደግሞ እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም።
ሐዲሡን ያወራው አባን ቢን ዑስማንን በወቅቱ የሰውነቱ ግማሽ ሽባ የመሆን በሽታ አጋጥሞት ስለነበር ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም በግርምት አይን ተመለከተው። አባንም ለሰውዬው እንዲህ አለው "እንደዚህ የምትመለከተኝ ምን ሆነህ ነው? በአለህ እምላለሁ! በዑሥማንም ላይ አልዋሸሁም። ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ አልዋሸም። ነገር ግን ይህ በሽታ ባጋጠመኝ እለት አላህ እንድለው አልወሰነልኝም ነበር። የሚያስቆጣ ነገር አጋጠመኝና እነዚህን የተጠቀሱ ቃላቶች ማለትን ዘነጋሁኝ።"