+ -

عَنْ أُمِّ عَطِيَّةَ رَضيَ اللهُ عنها أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا تُحِدُّ امْرَأَةٌ عَلَى مَيِّتٍ فَوْقَ ثَلَاثٍ إِلَّا عَلَى زَوْجٍ أَرْبَعَةَ أَشْهُرٍ وَعَشْرًا، وَلَا تَلْبَسُ ثَوْبًا مَصْبُوغًا إِلَّا ثَوْبَ عَصْبٍ، وَلَا تَكْتَحِلُ، وَلَا تَمَسُّ طِيبًا إِلَّا إِذَا طَهُرَتْ نُبْذَةً مِنْ قُسْطٍ أَوْ أَظْفَارٍ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 938]
المزيــد ...

ከኡሙ ዐጢየህ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል:
"አንዲት ሴት ከባሏ ውጪ ለሞተባት ሰው ሀዘንን ለመግለፅ ብላ ከሶስት ቀን በላይ መዋብን አትተው። የሞተባት ባሏ ከሆነ ግን አራት ወር ከአስር ቀን ከመዋብ ትታቀብ። (ለባሏ ሀዘን ስትቀመጥ) ከስፌት በፊት የተቀለመን ልብስ ካልሆነ በቀር በቀለም ያጌጠን ልብስ አትልበስ፣ አትኳል፣ ከወር አበባዋ ስትፀዳ ብቻ ቁራጭ የቀበርቾ ወይም የአዝፋር ሽቶን ከመቀባት ውጪ ሽቶንም አትቀባ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 938]

ትንታኔ

ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሴቶችን አባትም ይሁን ወይም ወንድምም ይሁን ወይም ልጅ ወይም ሌላ ለማንኛውም ለሞተ ሰው ሀዘንን ለመግለፅ ብለው ከሶስት ቀን በላይ መዋብን መተዋቸውን ከለከሉ። መዋብን መተው ሲባል ሽቶ መቀባት፣ ኩል መኳል፣ ማጌጥ፣ ቆንጆ ልብስ መልበስ ማለት ነው። የሞተው ባል ከሆነ ግን አራት ወር ከአስር ቀን መዋብን በመተው ሀዘኗን ትገልፃለች። ለባሏ ሃዘን ስትቀመጥ የ"ዐስብ" ልብስ በቀር ለውበት ተብሎ የተቀለሙን ሁሉ ልብሶች አትለብስም። የዐስብ ልብስ የሚባለው ከስፌት በፊት የሚቀለም የየመን ልብስ ነው። ለውበት ብላ ዓይኗን አትኳልም። ጥሩ መአዛ ያላቸውን ሽቶዎችም ይሁን ሌላ አትቀባም። ነገር ግን ከወር አበባዋ ጨርሳ ስትታጠብ የቀበርቾን ወይም የ"አዝፋር"ን ትንሽዬ ቁራጭ እጣን ቀላቅላ ትታጠባለች። እነዚህ ሁለቱ የታወቁ የእጣን አይነቶች ሲሆኑ ክልከላው ላይ የተጠቀሰው የሽቶዎች መደብ ውስጥ አይካተቱም። ከወር አበባ ለምትታጠብ ሴት የተፈቀደውም ደሙን ተከትሎ የሚመጣውን የብልት መጥፎ ጠረን ለማስወገድ ነው እንጂ ሽቶ ለመቀባት ታልሞ አይደለም።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ኢሕዳድ ማለት: ጌጥንና ወደ ጋብቻ የሚጋብዝን ውበት መተው ማለት ነው። አንዲት ሴት ሁሉንም ጌጥ፣ ሁሉንም ሽቶ፣ ኩልና ሁሉንም የውበት ልብሶች መራቅ ይኖርባታል።
  2. አንዲት ሴት ከባሏ ውጪ ለሞተባት ከሶስት ቀን በላይ ሃዘንን ለመግለፅ ብላ መዋብን ከመተው መከልከሏን እንረዳለን።
  3. የባል ደረጃ መገለፁን እንመለከታለን። ይህም ከባል ውጪ ከሶስት ቀን በላይ ማለፍ አይቻልምና ነው።
  4. ሶስት ቀንና ከዛ በታች ለሃዘን ብሎ መዋብን መተው መፈቀዱ ነፍስን ያሳርፋል።
  5. ሴት ልጅ እስካላረገዘች ድረስ አራት ወር ከአስር ቀን በባሏ ሞት ሰበብ መዋብን መተዋ ግዴታ ነው። እርጉዝ ከሆነች ግን ስትወልድ ነው የምታጠናቅቀው።
  6. ከውበት ውጪ የተቀለመ ልብስ መልበስ ይፈቀድላታል። ለውበት ነው የተቀለመው ወይስ አይደለም የሚለው የሚተረጎመው በአካባቢው ተለምዷዊ ፍቺ ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ