عن ابن عمر رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«أحْفُوا الشَّوَارِبَ وأَعْفُوا اللِّحَى».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 259]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ቀድሞ ቀመስን (ከአፍንጫ ስር ያለውን ፂም) አሳጥሩ ሪዛችሁን (የመንጋጭላ ፂማችሁን) ልቀቁ!"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 259]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀድሞ ቀመስን መቁረጥና አለመልቀቅን አዘዙ። እንደውም በደንብ መቁረጥ እንዳለበት ገለፁ።
በተቃራኒው ሪዝን (የመንጋጭላን ፂም) መልቀቅና እንደበዛ መተውን አዘዙ።