عَنْ حُذَيْفَةَ رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا قَامَ مِنَ اللَّيْلِ يَشُوصُ فَاهُ بِالسِّوَاكِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 245]
المزيــد ...
ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሊት የተነሱ ጊዜ አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁ ነበር።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 245]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አብዝተው የሚፍቁና በመፋቅም ላይ የሚያዙ ነበሩ። አንዳንድ ወቅቶች ላይም አጠንክረው ሱናውን ይተገብሩ ነበር። ከነዛም ወቅቶች መካከል: ሌሊት በሚቆሙበት ወቅት መፋቅ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁና ያፀዱ ነበር።