عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَامَ بَعْدَ أَنْ رَجَمَ الْأَسْلَمِيَّ فَقَالَ:
«اجْتَنِبُوا هَذِهِ الْقَاذُورَةَ الَّتِي نَهَى اللَّهُ عَنْهَا فَمَنْ أَلَمَّ فَلْيَسْتَتِرْ بِسِتْرِ اللَّهِ وَلْيُتُبْ إِلَى اللَّهِ، فَإِنَّهُ مَنْ يُبْدِ لْنَا صَفْحَتَهُ نُقِمْ عَلَيْهِ كِتَابَ اللَّهِ عز وجل».
[صحيح] - [رواه الحاكم والبيهقي] - [المستدرك على الصحيحين: 7615]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የአስለሚዩን ሰውዬ በድንጋይ ወግረው ከገደሉ በኋላ ተነስተው እንዲህ አሉ:
"አላህ ከርሱ የከለከለውን ይህን ቆሻሻ ድርጊት ራቁ። ይህን ድርጊት ከፈፀመም አላህ (ወንጀሉን) እንደሸሸገለት ይሸሽገው፤ ወደ አላህም ይመለስ። ወንጀሉን ለኛ ግልፅ የሚያደርግ ሰውም በአላህ መጽሐፍ መሰረት (ቅጣቱን) እንፈፅምበታለን።"
[ሶሒሕ ነው።] - [Al-Bayhaqi - Al-Haakim] - [አልሙስተድረክ ዓለስሶሒሐይን - 7615]
ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ማዒዝ ቢን ማሊክ አልአስለሚይን ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዝሙት ቅጣት በድንጋይ ወግረው ከገደሉት በኋላ ተነሱና ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ: አላህ የከለከላቸው የሆኑትን እነዚህን ቆሻሻ፣ ፀያፍና አስቀያሚ ወንጀሎች ራቁ። ከነዚህ ወንጀሎች አንዳችን የፈፀመ ካለም ሁለት ነገር መፈፀም ይጠበቅበታል: የመጀመሪያው: አላህ ወንጀሉን እንደሸሸገለት ተሸሽጎ ወንጀሉን አለመናገር። ሁለተኛው: ወደ አላህ ተውበት በማድረግ መቻኮል፣ በርሱ ላይ አለመዘውተር ነው። ወንጀሉ ለኛ ግልፅ የሆነችበት ሰው በርሱ ላይ በአላህ መጽሐፍ መሰረት ለዚህች ወንጀሉ የተጠቀሰውን ቅጣት እንፈፅምበታለን።