عن عرفجة رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول:
«مَنْ أَتَاكُمْ وَأَمْرُكُمْ جَمِيعٌ عَلَى رَجُلٍ وَاحِدٍ، يُرِيدُ أَنْ يَشُقَّ عَصَاكُمْ، أَوْ يُفَرِّقَ جَمَاعَتَكُمْ، فَاقْتُلُوهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1852]
المزيــد ...
ከዐርፈጀህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ:
"ጉዳያችሁ በአንድ መሪ የተሰበሰበ ሁኖ ሳለ አንድነታችሁን ሊሰነጥቅ ወይም ህብረታችሁን ሊበታትን የመጣ ሰውን ግደሉት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1852]
ሙስሊሞች በአንድ መሪና በአንድ ህብረት የተሰበሰቡ ሆነው ሳለ ከዚያም መሪነቱን መገዳደር ፈልጎ ወይም ሙስሊሞችን ከአንድ ህብረት በላይ እንዲሆኑ መበታተን ፈልጎ የመጣን ሰው አደጋውን ለመከላከልና የሙስሊሞችን ደም ለመጠበቅ ሲባል በነርሱ ላይ መከልከልና መጋደል ግዴታ እንደሆነ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።