عَنْ أُمِّ سَلَمَةَ أُمِّ المُؤمنين رضي الله عنها: أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«سَتَكُونُ أُمَرَاءُ فَتَعْرِفُونَ وَتُنْكِرُونَ، فَمَنْ عَرَفَ بَرِئَ، وَمَنْ أَنْكَرَ سَلِمَ، وَلَكِنْ مَنْ رَضِيَ وَتَابَعَ» قَالُوا: أَفَلَا نُقَاتِلُهُمْ؟ قَالَ: «لَا، مَا صَلَّوْا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1854]
المزيــد ...
ከኡሙ ሰለማ ኡሙል ሙእሚኒን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"እነሆ በናንተ ላይ መሪዎች ይሾማሉ። የምታውቁትንም የምታወግዙትንም ስራ ይሰራሉ። (የሚሰሩትን ውግዝ ስራ) የጠላ ሰው (ከወንጀል) ጠራ። ያወገዘም ሰው ሰላም ሆነ። ነገር ግን (የነሱን ውግዝ ተግባር) የወደደና የተከተለ (ወንጀል ውስጥ ወደቀ)" ሶሓቦችም "ታዲያ አንዋጋቸውምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም "ሶላትን እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም (እንዳትዋጓቸው!)" ብለው መለሱ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1854]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኛ ላይ መሪዎች እንደሚሾሙና ከፊል ስራዎቻቸው ከሸሪዓ ጋር የተስማማ ስለሆነ መልካም እንደምንለውና፤ ከፊሉን ደግሞ ከሸሪዓ ጋር ስለሚፃረር እንደምናወግዘው ተናገሩ። ውግዝ ተግባሮቻቸውን ማውገዝ ያልቻለና በቀልቡ የጠላ ሰው በርግጥም ከወንጀልና ንፍቅና ጠራ። በእጁ ወይም በአንደበቱ ማውገዝ የቻለ ሰውና በነርሱ ላይ ይህንን ያወገዘ በርግጥ ከወንጀልና ከወንጀል ተባባሪነት ሰላም ሆኗል። ነገር ግን ድርጊታቸውን የወደደና በርሱ ላይ የተከተላቸው እነርሱ እንደጠፉት ይጠፋል።
ከዚያም ሶሐቦች ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይህን አይነት ባህሪ የተላበሱ መሪዎችን አንዋጋምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "በመካከላችሁ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም እንዳትዋጓቸው!" በማለት ከዚህ ከለከሏቸው።