عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَا مِنْ نَبِيٍّ بَعَثَهُ اللهُ فِي أُمَّةٍ قَبْلِي إِلَّا كَانَ لَهُ مِنْ أُمَّتِهِ حَوَارِيُّونَ، وَأَصْحَابٌ يَأْخُذُونَ بِسُنَّتِهِ وَيَقْتَدُونَ بِأَمْرِهِ، ثُمَّ إِنَّهَا تَخْلُفُ مِنْ بَعْدِهِمْ خُلُوفٌ يَقُولُونَ مَا لَا يَفْعَلُونَ، وَيَفْعَلُونَ مَا لَا يُؤْمَرُونَ، فَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِيَدِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ، وَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِلِسَانِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ، وَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِقَلْبِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ، وَلَيْسَ وَرَاءَ ذَلِكَ مِنَ الْإِيمَانِ حَبَّةُ خَرْدَلٍ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 50]
المزيــد ...
ከዓብደላህ ቢን መስዑድ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ከኔ በፊት በነበሩት ህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ለርሱ ከህዝቦቹ መካከል ሱናውን (ፈለጉን) የሚይዙና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያትና ባልደረቦች አሉት። ከነርሱ በኋላ ግን የማይሰሩትን የሚናገሩና ያልታዘዙትን የሚሰሩ ምትኮች ይተካሉ። በእጁ የታገላቸውም እርሱ አማኝ ነው። በምላሱ የታገላቸውም እርሱ አማኝ ነው። በቀልቡ የታገላቸውም እርሱ አማኝ ነው። ከዚህ ውጪ ግን የጎመንዘር ዘለላ ያህል እንኳ ኢማን የለም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 50]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከርሳቸው በፊት አላህ በህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ከህዝቦቹ መካከል የተመረጡ፣ ረዳቶች፣ ታጋዮች፣ ታማኞች፣ ከርሱ በኋላ ለተተኪነት የሚበጁ፣ ፈለጉን የሚይዙና ትእዛዙንም የሚከተሉ ባልደረቦች ይኖሩታል፤ ከዚያም ከነዚህ መልካም አበዎች በኋላ ግን ምንም መልካም የሌላቸው የማይሰሩትን የሚናገሩና ያልታዘዙትን የሚሰሩ ሰዎች ይመጣሉ። በእጁ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። በምላሱ የታገላቸው እርሱም አማኝ ነው። በቀልቡም የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። ከዚህ ውጪ የሆነ ሰው ግን የጎመንዘር ፍሬ ያህል እንኳ ኢማን እንደሌለው ተናገሩ።