+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤمنينَ رضي الله عنها قَالَتْ:
كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ كِلاَنَا جُنُبٌ، وَكَانَ يَأْمُرُنِي، فَأَتَّزِرُ، فَيُبَاشِرُنِي وَأَنَا حَائِضٌ، وَكَانَ يُخْرِجُ رَأْسَهُ إِلَيَّ وَهُوَ مُعْتَكِفٌ فَأَغْسِلُهُ وَأَنَا حَائِضٌ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 299]
المزيــد ...

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦
"እኔና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለታችንም ጀናባ ላይ ሆነን ከአንድ እቃ እየጨለፍን እንታጠብ ነበር። የወር አበባ ላይ በሆንኩ ወቅትም ሽርጥ እንዳደርግ ያዙኝና ከግንኙነት ውጪ የሆነን ጨዋታ እንጫወት ነበር። ኢዕቲካፍ ላይ በሆኑ ወቅት ጭንቅላታቸውን ወደኔ ያወጡልኝና የወር አበባ ላይ ሆኜም አጥባቸው ነበርኩ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 299]

ትንታኔ

የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ስለነበራት አንዳንድ ግላዊ ሁኔታዋ ተናገረች። ከዚህም ውስጥ: የጀናባ ትጥበትን ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሁለቱም ከአንድ እቃ እየጨለፉ ይታጠቡ ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የወር አበባ ላይ ሆና ሳለ ለጨዋታ መቅረብ የፈለጉ ጊዜ ከእንብርት እስከ ጉልበቷ ያለውን ሰውነት እንድትሸፍን ያዟትና ከግንኙነት ውጪ ያለን ጨዋታ ይጫወቱ ነበር። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ ይገቡ ነበር። እናታችን ዓኢሻ በቤቷ ውስጥ የወር አበባ ላይ ሆና ሳለ ጭንቅላታቸውን ያወጡላትና ታጥባቸው ነበር።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንድ ወንድ ከሚስቱ ጋር ከአንድ እቃ እየጨለፈ መታጠብ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  2. የወር አበባ ላይ ያለችን ሚስቱ ከብልቷ ውጪ የፍቅር ጫወታ እንደሚፈቀድና ሰውነቷም ንፁህ እንደሆነ እንረዳለን።
  3. ከግንኙነት ውጪ ያለን ፍቅር በሚሰሩበት ወቅት ሽርጥ መልበሷ እንደሚወደድም እንረዳለን።
  4. ወደ ክልክል ከመውደቅ የሚከለክሉ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።
  5. የወር አበባ ላይ ያለች ሴት መስጂድ መቀመጥ መከልከሏን እንረዳለን።
  6. የወር አበባ ላይ ያለች ሴት እርጥብም ሆነ ደረቅ ነገሮችን መንካቷ እንደሚፈቀድ እንረዳለን። ከዚህም ውስጥ ፀጉርን ማጠብና ማበጠሯ ለአብነት ይጠቀሳል።
  7. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከቤተሰባቸው ጋር የነበራቸውን መልካም አኗኗር እንረዳለን።