عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رضي الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«أُعْطِيتُ خَمْسًا لَمْ يُعْطَهُنَّ أَحَدٌ قَبْلِي: نُصِرْتُ بِالرُّعْبِ مَسِيرَةَ شَهْرٍ، وَجُعِلَتْ لِي الأَرْضُ مَسْجِدًا وَطَهُورًا، فَأَيُّمَا رَجُلٍ مِنْ أُمَّتِي أَدْرَكَتْهُ الصَّلاَةُ فَلْيُصَلِّ، وَأُحِلَّتْ لِي المَغَانِمُ، وَلَمْ تَحِلَّ لِأَحَدٍ قَبْلِي، وَأُعْطِيتُ الشَّفَاعَةَ، وَكَانَ النَّبِيُّ يُبْعَثُ إِلَى قَوْمِهِ خَاصَّةً وَبُعِثْتُ إِلَى النَّاسِ عَامَّةً».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 335]
المزيــد ...
ከጃቢር ቢን ዓብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ከኔ በፊት አንድም አካል ያልተሰጠው አምስት ነገሮችን ለኔ ተሰጥተውኛል። የወር መንገድ ሲቀር (ጠላቶች ውስጥ) ፍርሃት በመክተት ተረድቻለሁ፤ ምድር ለኔ መስገጃም ንፅህና መጠበቂያም ተደርጋልኛለች። ስለዚህ ከኡመቴ ማንኛውም ሰው ሶላት ከደረሰችበት ይስገድ። ምርኮ ለኔ ተፈቅዷል፤ ከኔ በፊት ለአንድም አካል አልተፈቀደችም። ምልጃ ተሰጥቶኛል። ነቢይ የሚላከው ወደ ህዝቦቹ ብቻ ነበር። እኔ ግን ወደ ሰው ባጠቃላይ ተልኬያለሁ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 335]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከርሳቸው በፊት ለነበረ ለአንድም ነቢይ ያልተሰጡ አምስት ነገሮች አላህ ለርሳቸው እንደሰጠ ተናገሩ:
የመጀመሪያው: በፍርሃት ተረድቼያለሁ። በኔና በነርሱ መካከል የወር መንገድ ቢቀር ራሱ የጠላቶቼን ልብ ፍርሃት ይወራቸዋል።
ሁለተኛው: ምድር ለኛ መስጂድ ተደርጋለች። የትም ብንሆን እንሰግዳለን። ውሃ መጠቀም በተሳነን ጊዜ ደሞ አፈሯ መፅጃ ተደርጎልናል።
ሶስተኛ: ለኛ የጦርነት ምርኮ ተፈቅዶልናል። ይህም ሙስሊሞች ከከሃዲዎች ጋር በሚያደርጉት ጦርነት የሚማርኩት ንብረት ነው።
አራተኛ: ሰዎችን ከትንሳኤ ቀን መቆም ጭንቀት የምገላግልበት ትልቁ ምልጃ ተሰጥቶኛል።
አምስተኛ: ወደ ፍጡራን ባጠቃላይ ወደ ሰዉም ወደ ጂኑም ሁሉ ተልኬያለሁ። ይህም ከርሳቸው በፊት ከነበሩት ነቢያት ተቃራኒ መሆኑ ነው። እነርሱ ይላኩ የነበሩት ወደ ህዝባቸው ብቻ ነበርና።