عَنْ حُذَيْفَةَ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
كُنَّا إِذَا حَضَرْنَا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَعَامًا لَمْ نَضَعْ أَيْدِيَنَا حَتَّى يَبْدَأَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَيَضَعَ يَدَهُ، وَإِنَّا حَضَرْنَا مَعَهُ مَرَّةً طَعَامًا، فَجَاءَتْ جَارِيَةٌ كَأَنَّهَا تُدْفَعُ، فَذَهَبَتْ لِتَضَعَ يَدَهَا فِي الطَّعَامِ، فَأَخَذَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِيَدِهَا، ثُمَّ جَاءَ أَعْرَابِيٌّ كَأَنَّمَا يُدْفَعُ فَأَخَذَ بِيَدِهِ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «إِنَّ الشَّيْطَانَ يَسْتَحِلُّ الطَّعَامَ أَنْ لَا يُذْكَرَ اسْمُ اللهِ عَلَيْهِ، وَإِنَّهُ جَاءَ بِهَذِهِ الْجَارِيَةِ لِيَسْتَحِلَّ بِهَا فَأَخَذْتُ بِيَدِهَا، فَجَاءَ بِهَذَا الْأَعْرَابِيِّ لِيَسْتَحِلَّ بِهِ فَأَخَذْتُ بِيَدِهِ، وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، إِنَّ يَدَهُ فِي يَدِي مَعَ يَدِهَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2017]
المزيــد ...
ከሑዘይፋ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ማዕድ ለመጋራት የተገኘን ጊዜ የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጃቸውን ወደ ማዕዱ ከመስደዳቸውና (ከመጀመራቸው) በፊት እኛ እጃችንን አንሰድም ነበር። አንድ ቀን ከርሳቸው ጋር ማዕድ ለመጋራት ተገኘን። (ከፍጥነቷ የተነሳ) ልክ እየተገፈተረች በሚመስል መልኩ የሆነች አንዲት ልጅ መጣችና እጇን ወደ ማዕዱ ሰደደች። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጇን ያዟት። ቀጥሎም (ከፍጥነቱ የተነሳ) ልክ እየተገፈተረ በሚመስል መልኩ አንድ የገጠር ሰውዬ መጣና እጁን ወደ ማዕዱ ሰደደ። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እሱንም እጁን ያዙትና እንዲህ አሉ: "ሸይጧን የአላህ ስም እንዳይወሳበት በማድረግ ምግቡን ለራሱ የተመቸ ያደርገዋል። እርሱም ይህቺን ሴትዮ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞ መጣ። እጇንም ያዝኳት። ይህንንም ሰውዬ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞ መጣ። እጁንም ያዝኩት። ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የሸይጧንን እጅ ከሴትዮዋ እጅ ጋር ይዤዋለሁ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2017]
ሑዘይፋ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት: ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ማዕድ ለመጋራት በተገኙ ጊዜ የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጃቸውን ወደ ማዕዱ ከመስደዳቸውና ከመጀመራቸው በፊት እነርሱ እጃጀውን አይሰዱም ነበር። አንድ ቀን ከርሳቸው ጋር ማዕድ ለመጋራት ተገኘን። ከፍጥነቷ የተነሳ አመጣጧ ልክ እየተገፈተረች በሚመስል መልኩ የሆነች አንዲት ሴትዮ መጣችና እጇን ወደ ማዕዱ ሰደደች። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጇን ያዟት። ቀጥሎም ከፍጥነቱ የተነሳ አመጣጡ ልክ እየተገፈተረ በሚመስል መልኩ የሆነ አንድ የገጠር ሰውዬ መጣና እጁን ወደ ማዕዱ ሰደደ። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምግቡን ከመንካቱ በፊት እጁን ያዙትና እንዲህ አሉ: "ሰውዬው የአላህ ስም ሳይወሳበት ምግቡን የጀመረ ጊዜ ሸይጧን ምግቡን ለመመገብ ይመቻቻል። እርሱም ይህቺን ሴትዮ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዟት መጣ። እጇንም ያዝኳት። ይህንንም ሰውዬ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞት መጣ። እጁንም ያዝኩት። ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የሸይጧንን እጅ ከሴትዮዋ እጅ ጋር በእጄ ነው።" ካሉ በኋላ የአላህን ስም ካወሱ በኋላ ተመገቡ።