عَنْ عُثْمَانَ الشَّحَّامِ، قَالَ: انْطَلَقْتُ أَنَا وَفَرْقَدٌ السَّبَخِيُّ إِلَى مُسْلِمِ بْنِ أَبِي بَكْرَةَ وَهُوَ فِي أَرْضِهِ، فَدَخَلْنَا عَلَيْهِ فَقُلْنَا: هَلْ سَمِعْتَ أَبَاكَ يُحَدِّثُ فِي الْفِتَنِ حَدِيثًا؟ قَالَ: نَعَمْ، سَمِعْتُ أَبَا بَكْرَةَ رضي الله عنه يُحَدِّثُ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّهَا سَتَكُونُ فِتَنٌ، أَلَا ثُمَّ تَكُونُ فِتْنَةٌ الْقَاعِدُ فِيهَا خَيْرٌ مِنَ الْمَاشِي فِيهَا، وَالْمَاشِي فِيهَا خَيْرٌ مِنَ السَّاعِي إِلَيْهَا، أَلَا فَإِذَا نَزَلَتْ أَوْ وَقَعَتْ فَمَنْ كَانَ لَهُ إِبِلٌ فَلْيَلْحَقْ بِإِبِلِهِ، وَمَنْ كَانَتْ لَهُ غَنَمٌ فَلْيَلْحَقْ بِغَنَمِهِ، وَمَنْ كَانَتْ لَهُ أَرْضٌ فَلْيَلْحَقْ بِأَرْضِهِ»، قَالَ فَقَالَ رَجُلٌ: يَا رَسُولَ اللهِ أَرَأَيْتَ مَنْ لَمْ يَكُنْ لَهُ إِبِلٌ وَلَا غَنَمٌ وَلَا أَرْضٌ؟ قَالَ: «يَعْمِدُ إِلَى سَيْفِهِ فَيَدُقُّ عَلَى حَدِّهِ بِحَجَرٍ، ثُمَّ لِيَنْجُ إِنِ اسْتَطَاعَ النَّجَاءَ، اللهُمَّ هَلْ بَلَّغْتُ؟ اللهُمَّ هَلْ بَلَّغْتُ؟ اللهُمَّ هَلْ بَلَّغْتُ؟»، قَالَ: فَقَالَ رَجُلٌ: يَا رَسُولَ اللهِ أَرَأَيْتَ إِنْ أُكْرِهْتُ حَتَّى يُنْطَلَقَ بِي إِلَى أَحَدِ الصَّفَّيْنِ، أَوْ إِحْدَى الْفِئَتَيْنِ، فَضَرَبَنِي رَجُلٌ بِسَيْفِهِ، أَوْ يَجِيءُ سَهْمٌ فَيَقْتُلُنِي؟ قَالَ: «يَبُوءُ بِإِثْمِهِ وَإِثْمِكَ، وَيَكُونُ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2887]
المزيــد ...
ከዑሥማን አሽሸሓም እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «እኔና ፈርቀድ አስሰበኺይ ወደ ሙስሊም ቢን አቢ በክራ መኖሪያ እርሱም መሬቱ ላይ ሳለ ሄድን። እርሱም ዘንድ ገባንና: "አባትህ ስለ ፈተና ሐዲሥ ሲናገር ሰምተሀዋልን?" አልነው። እርሱም እንዲህ አለ: ‹አዎን! አባ በክራን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ ብሎ ሲያወራ ሰምቼዋለሁ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:-
'አዋጅ! ፈተና ትኖራለች። አዋጅ! ቀጥሎም በዛች ፈተና ከተራማጅ ተቀማጭ የተሻለ የሚሆንባት፤ ወደ ፈተናዋ ከሚሮጥ የሚራመድ የተሻለ የሚሆንባት ፈተና ትከሰታለች። አዋጅ! ይህቺ ፈተና እውን የሆነች ወይም የተከሰተች ጊዜ ለርሱ ግመል ያለው ሰው ወደ ግመሉ ይጠጋ! ለርሱ ፍየል ያለውም ሰው ወደ ፍየሉ ይጠጋ! ለርሱ መሬት ያለውም ሰው ወደ መሬቱ ይጠጋ!' አንድ ሰውዬም እንዲህ በማለት ጠየቃቸው 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩን ግመልም፣ ፍየልም፣ መሬትም የሌለው ሰውስ ወደየት ይጠጋ?' እርሳቸውም 'ወደ ሰይፉ ያምራና ስለቱን በድንጋይ ይስበር። ከዚያም በመሸሽ መዳን ከቻለ ይሽሽ! አላህ ሆይ! አድርሻለሁኝን? አላህ ሆይ! አድርሻለሁኝን?' አሉ። አንድ ሰውዬም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩኝ አስገድደው ወደ አንዱ ጎራ ወይም አንዱ ቡድን ላይ ቢወስዱኝና አንዱ በሰይፉ ቢመታኝ ወይም ቀስት መጥቶ ቢወጋኝስ (ወንጀል ይኖርብኛልን?)' በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም: 'ያንተም የራሱንም ወንጀል ወደርሱ ይመለሳል። ከእሳት ጓዶችም ይሆናል።' አሉት።›"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2887]
ዑሥማን አሽሸሓምና ፈርቀድ አስሰብኺይ የታላቁ ሶሓቢይ የአቢ በክራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ልጅ የሆነው ሙስሊም ዘንድ አባቱ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሙስሊሞች መካከል ስለሚኖር የርስበርስ ፈተናና ጦርነት ሰምቶ ሲያወራ ከሰማ እንዲነግራቸው ሊጠይቁት ሄዱ። እርሱም አዎን! ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሳቸው ከሞቱ በኋላ ፈተና እንደሚኖር ይህ ፈተናም በሚከሰት ጊዜም ይህንን ፈተና ችላ ብሎ የተቀመጠ ወደርሷ ከሚራመድ ይበልጣል። ምክንያቱም ቁጭ ያለው አይሳተፍባትምም ስለርሷም አይመራመርምና። ወደርሷ የሚራመድም ወደርሷ ለመመርመርና ለመሳተፍ ከሚሮጠው የተሻለ መሆኑን ተናገሩ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በርሱ ዘመን ፈተናዋ የተከሰተችበት ወይም ያጋጠመችው ሰው የሚጠጋበት ስፍራ ካገኘ ወደዛ እንዲሸሽ እንዲህ በማለት ጥቆማ ሰጡ: ለርሱ የምትሰማራ ግመል ያለው ወደ ግመሉ ይጠጋ፤ ለርሱ የምትሰማራ ፍየል ያለው ሰው ወደ ፍየሉ ይጠጋ፤ ለርሱ መሬት፣ እርሻ ያለው ሰው ወደ መሬቱ ይጠጋ። አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ግመልም፣ ፍየልም፣ መሬትም የሌለው ሰው ወደየት ይጠጋ?" እርሳቸውም "ወደ መሳሪያው ያምራና ይስበረው ያዶምዱመው ከዚያም መሸሽ ከቻለ ነፍሱንና ልጁን ይዞ ይሽሽ።" አሉ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶስት ጊዜ እንዲህ በማለት አላህን ምስክር አደረጉ: "አላህ ሆይ! መልዕክትህን አደረስኩኝን? አላህ ሆይ! መልዕክትህን አደረስኩኝን? አላህ ሆይ! መልዕክትህን አደረስኩኝን?" አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከሁለቱ ቡድኖች ወይም ጭፍራዎች አንዱን እንድቀላቀል ብገደድና አንዱ በሰይፉ ቢመታኝ ወይም ቀስት መጥቶ ቢገድለኝ ወንጀል ይኖርብኛልን?" አላቸው። እርሳቸውም "የራሱና የተገደለው ሰው ወንጀል ወደርሱ ይመለሳል። የትንሳኤ ቀንም ከእሳት ጓዶች ይሆናል።"