+ -

عَنْ عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«الذَّهَبُ بِالذَّهَبِ، وَالْفِضَّةُ بِالْفِضَّةِ، وَالْبُرُّ بِالْبُرِّ، وَالشَّعِيرُ بِالشَّعِيرِ، وَالتَّمْرُ بِالتَّمْرِ، وَالْمِلْحُ بِالْمِلْحِ، مِثْلًا بِمِثْلٍ، سَوَاءً بِسَوَاءٍ، يَدًا بِيَدٍ، فَإِذَا اخْتَلَفَتْ هَذِهِ الْأَصْنَافُ، فَبِيعُوا كَيْفَ شِئْتُمْ، إِذَا كَانَ يَدًا بِيَدٍ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1587]
المزيــد ...

ከዑባዳህ ቢን ሷሚት - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ወርቅን በወርቅ፣ ብርን በብር፣ ስንዴን በስንዴ፣ ገብስን በገብስ፣ ተምርን በተምር፣ አሞሌን በአሞሌ (ስትለዋወጡ) አምሳያውን በአምሳያው፣ እኩል በእኩል፣ እጅ በእጅ መሆን አለበት። የገንዘብ አይነቶቹ (የምትለዋወጡት) የተለያዩ ከሆኑ ግን እጅ በእጅ እስከሆነ ድረስ እንደፈለጋችሁ ሽጡ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1587]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አራጣ በሚገባባቸው ስድስቱ የገንዘብ አይነቶች ዙሪያ ትክክለኛውን የመገበያያ መንገድ ገለፁ። እነርሱም: ወርቅ፣ ብር፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ተምርና ጨው (አሞሌ) ናቸው። ተመሳሳይ የሆኑ ገንዘቦችን በተመሳሳይ ገንዘብ መለዋወጥ ከሆነ ወርቅን በወርቅ፣ ብርን በብር ... ለመሳሰሉት የግድ ሁለት መስፈርቶች መሟላት አለባቸው: የመጀመሪያው: እንደወርቅና ብር በሚዛን የሚመዘኑ ከሆነ ሚዛናቸው ተመሳሳይ መሆን አለበት። ወይም እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ ተምርና ጨው በስፍር የሚሰፈሩ ከሆኑ ደሞ የስፍር ልካቸው ተመሳሳይ መሆን አለበት። ሁለተኛው: ሻጩ ገንዘቡን ገዢ ሸቀጡን መውሰዳቸው ነው። ይህም የሚሆነው ንግዱ በተፈፀመበት ቦታ ነው። መለዋወጡ ወርቅን በብር መለዋወጥ፣ ተምርን በስንዴ መለዋወጥ ይመስል የገንዘብ አይነቶቹ በተለያዩበት ከሆነ ግን አንድ መስፈርት ብቻ ከተሟላ በቂ ነው። እርሱም ሻጩ ገንዘቡን ገዢውም ሸቀጡን በግብይይቱ ስፍራ ላይ መውሰዳቸው ነው። ይህ ካልሆነ ግብይቱ የተበላሸ ነው። ክልክል የሆነው አራጣ ላይም ወድቀዋል። በዚህ ወንጀል ላይም ሻጩም ሆነ ገዢው እኩል ናቸው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ቬትናማዊ ሃውሳ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አራጣ የሚገባባቸው ገንዘቦችና እንዴት እንደምንገበያይባቸው መገለፁን፤
  2. አራጣዊ ግብይት መከልከሉን እንረዳለን።
  3. የወረቀት ገንዘቦች በአራጣ ጉዳይ የወርቅና ብርን ብይን ይይዛሉ።
  4. ስድስቱ አራጣ የሚመለከታቸው ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ ዙሪያ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ: 1 - አራጣ የሚመለከታቸውን ገንዘቦች እርስ በራሱ በተመሳሳይ አይነት መለዋወጥ ወርቅን በወርቅ፣ ተምርን በተምር ወዘተ መለዋወጥ ነው። ይህ ልውውጥ ትክክለኛ እንዲሆን ሁለት መስፈርቶች መሟላት አለባቸው። አንደኛ: ሚዛኑ ወይም ስፍሩ ተመሳሳይ መሆን ይኖርበታል። ሁለተኛ: በግብይይቱ ስፍራ መለዋወጥ ይኖርባቸዋል። 2 - አራጣ የሚመለከታቸው ገንዘቦች ሆነው አራጣ ያስባላቸው ምክንያት ተመሳሳይ ቢሆንም አይነታቸው ግን የተለያዩን ገንዘቦች መለዋወጥ ወርቅን በብር፣ ስንዴን በገብስ መለዋወጥን ይመስል። ለዚህ ልውውጥም በሁለቱም በኩል የሚለዋወጡት ገንዘብ እኩኩል መሆኑ መስፈርት አይደለም። በግብይቱ ስፍራ መቀባበላቸው ግን መስፈርት ነው። 3 - አራጣ የሚመለከታቸው ገንዘቦችን አይነታቸው የተለያየና አራጣ ያስባላቸው ምክንያትም የተለያየ የሆኑን መለዋወጥ። ወርቅን በተምር መለዋወጥን ይመስል። ለዚህም በግብይቱ ስፍራ መለዋወጥም ሆነ በሁለቱ ተለዋዋጮች በኩል ያለው ገንዘብ እኩኩል መሆኑ መስፈርት አይደለም።
  5. ሁለቱም አራጣ የማይመለከታቸው የሆኑ ገንዘቦችን ወይም አንዱ አራጣ የሚመለከተው ሌላኛው ደግሞ አራጣ የማይመለከተውን ገንዘብ ለመሸጥና ለመግዛት በግብይቱ ስፍራ መቀባበልም ሆነ እኩኩል መሆናቸው መስፈርት አይደለም። ለምሳሌ መሬትን በወርቅ መገበያየት ይመስል።