+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم أنه قال:
«مَنْ ‌خَرَجَ ‌مِنَ ‌الطَّاعَةِ، وَفَارَقَ الْجَمَاعَةَ فَمَاتَ، مَاتَ مِيتَةً جَاهِلِيَّةً، وَمَنْ قَاتَلَ تَحْتَ رَايَةٍ عِمِّيَّةٍ، يَغْضَبُ لِعَصَبَةٍ، أَوْ يَدْعُو إِلَى عَصَبَةٍ، أَوْ يَنْصُرُ عَصَبَةً، فَقُتِلَ، فَقِتْلَةٌ جَاهِلِيَّةٌ، وَمَنْ خَرَجَ عَلَى أُمَّتِي، يَضْرِبُ بَرَّهَا وَفَاجِرَهَا، وَلَا يَتَحَاشَى مِنْ مُؤْمِنِهَا، وَلَا يَفِي لِذِي عَهْدٍ عَهْدَهُ، فَلَيْسَ مِنِّي وَلَسْتُ مِنْهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1848]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"ከመሪ ትእዛዝ አምፆ በመውጣት የሙስሊሙን ህብረት ተለይቶ የሞተ የድንቁርና አሟሟት ሙቷል። ለወገኑ ሲል እየተቆጣ ወይም ወደ ወገንተኝነት እየተጣራ ወይም ወገን ለይቶ እየረዳ በዕውር ባንዲራ ስር እየተዋጋ ቢገደል የድንቁርና አሟሟት ሙቷል። በኡመቴ ላይ (ሊመራ) የወጣ መልካሙንም መጥፎውንም የሚማታ ስለአማኙ ህዝብ ምንም ደንታ የሌለው የቃል ኪዳን ባለቤት ለሆኑትም በቃል ኪዳኑ የማይሞላ ሰው ከኔም አይደለም እኔም ከርሱ አይደለሁም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1848]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመሪዎች ትእዛዝ አምፆ በመውጣት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከተስማሙበት መሪ ያፈነገጠ ሰው በዚህ ያለመታዘዝና አማፂነት ሁኔታ ላይ ሆኖ ቢሞት የእነዚያ መሪን የማይታዘዙ፣ ወደ አንድ ህብረት የማይጠጉ በተቃራኒ ቡድንተኛና ወገንተኛ ሁነው ከፊሉ ከፊሉን ይዋጉ የነበሩት የድንቁርና ዘመን ባለቤቶችን አይነት አሟሟት ሙቷል።
- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እውነተኛው ከውሸተኛው ባልተለየበት ባንዲራ ስር የተዋጋ ሰው ቁጣውና እምነቱ ሐቅን ለመርዳት ሳይሆን ለጠራ ህዝባዊ ወይም ጎሳዊ ወገንተኝነት የሆነ ፤ ያለእውቀትና እርግጠኝነት ለወገንተኝነት የሚዋጋ ሰው በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ከተገደለ ሞቱ እንደ ድንቁርና ዘመን ሞት ነው የሚሆነው ብለው ተናገሩ።
በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኡመት ላይ ለመሪነት የወጣ መልካሙንም መጥፎውንም የሚማታ፣ በሚፈፅመው ድርጊት ላይ ደንታ የሌለው፣ አማኞችን በመግደል የሚደርስበትን ቅጣት የማይፈራ፤ ከከሀዲያንና ከመሪዎች ጋር ያለውን ቃል ኪዳን ከመጠበቅ ይልቅ ቃል ኪዳኑን የሚያፈርስ (ይህ ትልቅ ወንጀለም ነው።) ይህን የሰራ ሰው ለዚህ ትልቅ ዛቻ የተገባ ይሆናል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህን ማመፅ ላይ እስካልሆነ ድረስ መሪዎችን መታዘዝ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  2. እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከመሪ ትእዛዝ የወጣና ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ያፈነገጠ ላይ ከባድ ማስጠንቀቂያ አለ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ቢሞት የድንቁርናው ዘመን ሰዎች መንገድ ላይ ሆኖ ሙቷል።
  3. ሐዲሡ ውስጥ ለወገንተኝነት ብሎ መዋጋት ክልክል መሆኑ ተገልጿል።
  4. ቃል ኪዳንን መሙላት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  5. መሪን በመታዘዝና አንድነትን በመጠበቅ ደህንነት፣ መረጋጋት፣ የሁኔታዎች መስተካከልና የመሳሰሉት ብዙ በጎ ነገሮች ይገኛሉ።
  6. ከድንቁርና ዘመን ባለቤቶች ሁኔታ ጋር መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን።
  7. የሙስሊሙን ህብረት አጥብቆ መያዝ መታዘዙን እንረዳለን።
ተጨማሪ