+ -

عَنْ بَهْزِ بْنِ حَكِيمٍ عَنْ أَبِيهِ عَنْ جَدِّهِ قَالَ:
قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ: مَنْ أَبَرُّ؟ قَالَ: «أُمَّكَ، ثُمَّ أُمَّكَ، ثُمَّ أُمَّكَ، ثُمَّ أَبَاكَ، ثُمَّ الْأَقْرَبَ فَالْأَقْرَبَ».

[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد] - [سنن أبي داود: 5139]
المزيــد ...

ከበህዝ ቢን ሐኪም ከአባቱ እንደተላለፈው: አባቱም ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ:
«"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ ከዚያም ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህ" አሉ።»

[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 5139]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሰዎች ሁሉ አስበልጠን በጎ ሊዋልለት፣ መልካም ሊሰራለት የሚገባው፣ ባማረ መልኩ ልንኗኗረው፣ ልንወዳጀውና ትስስራችንን ልናጠናክርለት የሚገባው በላጩ ሰው ማን እንደሆነ ገለፁ። እርሷም እናት ናት። ከሌሎች አካላቶች ሐቅ የእናት ሐቅ የበለጠ እንደሆነ ለማስገንዘብም ሶስት ጊዜ በመደጋገም አጽንዖት ሰጡት። ይህም የርሷ ደረጃ ከተቀሩት ሰዎች ባጠቃላይ እንደሚበልጥ ለመግለፅ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከእናት በመቀጠል በጎ ሊዋልለት የሚገባውን እንዲህ በማለት ገለፁ: ቀጥሎ አባት ቀጥሎ ቅርብ የሆኑ ዘመዶች አሉ። እጅግ ቅርብ በሆነ ቁጥር ሩቅ ከሆነው ዘመድ የበለጠ ዝምድናው ሊቀጠል ይገባል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሐዲሡ እናትን ማስቀደም እንደሚገባ ቀጥሎ አባትን ቀጥሎ ቅርብ ዘመዶችን እንደየቅርበታቸው ደረጃ ማስቀደም እንደሚገባ ያስረዳናል።
  2. የወላጆች ደረጃ በተለይ የእናት ደረጃ መገለፁን ተረድተናል።
  3. ሐዲሡ ውስጥ ለእናት በጎ መስራትን ሶስት ጊዜ ደጋገሙት። ይህም ለልጆቿ ያላት ችሮታ ከሌላው የሚበልጥ ስለሆነ፤ የእርግዝናን ቀጥሎ የመውለድን ቀጥሎ የማጥባትን ጭንቅ፣ ድካምና መከራ በማየት የምታሳልፍበት ጊዜ ስለሚበዛና በዚህም የምትሰቃየው ብቻዋን ስለሆነች ነው። ከዚያም ደግሞ የማነፁን ጉዳይ ከአባት ጋር ትጋራለች።