عن عبد الله بن عمرو رضي الله عنهما قال:
لَمْ يَكُنِ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَاحِشًا وَلَا مُتَفَحِّشًا، وَكَانَ يَقُولُ: «إِنَّ مِنْ خِيَارِكُمْ أَحْسَنَكُمْ أَخْلَاقًا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3559]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3559]
ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መካከል ፀያፍ መናገር ወይም ፀያፍ ድርጊት አይገኝም ነበር። ትዝም አይላቸው። እሳቸው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የላቀ ስነምግባር ባለቤት ነበሩ።
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ዘንድ ከናንተ መካከል በላጩ መልካምን በመለገስ፣ ፊቱን በመፍታት፣ ሰውን ከማወክ በመቆጠብና የነሱን ክፋት በመቻል እንዲሁም ሰዎች ጋር ባማረ መልኩ በመኗኗር ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።"