عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا:
أَنَّ رَجُلًا سَأَلَ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: أَيُّ الإِسْلاَمِ خَيْرٌ؟ قَالَ: «تُطْعِمُ الطَّعَامَ، وَتَقْرَأُ السَّلاَمَ عَلَى مَنْ عَرَفْتَ وَمَنْ لَمْ تَعْرِفْ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 12]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:-
"አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 12]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው በላጩ? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ሁለት ነገሮችን ጠቀሱ።
የመጀመሪያው: ድሃዎችን ማብላትን ማብዛት ነው። እዚህ ውስጥም ሶደቃ፣ ስጦታ፣ ግብዣ፣ የሰርግ ድግስ ይገባሉ። የማብላቱ በላጭነትም በረሃብና ኑሮ በተወደደበት ወቅት የጠነከረ ይሆናል።
ሁለተኛው: አወቅከውም አላወቅከውም በሁሉም ሙስሊም ላይ ሰላምታን ማቅረብ ነው።