+ -

عن أبي بَشير الأنصاري رضي الله عنه:
أَنَّهُ كَانَ مَعَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي بَعْضِ أَسْفَارِهِ، قَالَ: فَأَرْسَلَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَسُولًا -وَالنَّاسُ فِي مَبِيتِهِمْ-: «لَا يَبْقَيَنَّ فِي رَقَبَةِ بَعِيرٍ قِلَادَةٌ مِنْ وَتَرٍ أَوْ قِلَادَةٌ إِلَّا قُطِعَتْ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2115]
المزيــد ...

ከአቡ በሺር አል አንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው:
እርሱ በአንድ ጉዞ ላይ ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ነበርና እንዲህ አለ: "ሰዎች በማደሪያቸው ባሉበት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን የሚያውጅ) አንድ መልክተኛ ላኩ ' በግመል አንገት ላይ (የታሰረ) የቀስት ገመድ ወይም ገመድ የተቆረጠ ቢሆን እንጂ ምንም እንዳይቀር!'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2115]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ጉዞ ላይ ሰዎች በሚያድሩበት የግመልና የመኝታ ድንኳናቸው ስፍራቸው ውስጥ ባሉበት ወደ ሰዎች በግመል ላይ የምትንጠለጠል ገመድ እንድትቆረጥ የሚያዝ አንድን ሰው ላኩ። ይህም የቀስት ገመድም (ወተር) ይሁን ወይም ከርሱ ውጪ የቃጭልና የጫማ ገመድ የመሳሰሉም ቢሆን ተመሳሳይ ነው። ይህም የሰው አይን ፈርተው ያስሩት ስለነበር ነው። እንዲቆርጡት የታዘዙበት ምክንያትም ከነርሱ ላይ አንዳችም ነገር ስለማይመልስ ነው። ጥቅምና ጉዳት አጋር በሌለው በአላህ እጅ ብቻ ነውና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የቀስት ገመድና ማንኛውንም ገመድ ጥቅም ያመጣል ወይም ጉዳት ይከላከላል በሚል ማሰር ከሺርክ የሚመደብ ስለሆነ ክልክል ነው።
  2. ከቀስት ገመድ ውጪ ያሉ ገመዶችን ማሰር ለውበት ወይም እንስሳን ለመምራት ወይም በርሱ ለማሰር ከሆነ ችግር የለውም።
  3. መጥፎን በቻሉት መጠን ማውገዝ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  4. ልብን አጋር በሌለው አላህ ላይ ብቻ ማንጠልጠል ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ተጨማሪ