+ -

عَنْ أَبي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَا مِنْ صَاحِبِ ذَهَبٍ وَلَا فِضَّةٍ، لَا يُؤَدِّي مِنْهَا حَقَّهَا، إِلَّا إِذَا كَانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ، صُفِّحَتْ لَهُ صَفَائِحُ مِنْ نَارٍ، فَأُحْمِيَ عَلَيْهَا فِي نَارِ جَهَنَّمَ، فَيُكْوَى بِهَا جَنْبُهُ وَجَبِينُهُ وَظَهْرُهُ، كُلَّمَا بَرَدَتْ أُعِيدَتْ لَهُ، فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ، حَتَّى يُقْضَى بَيْنَ الْعِبَادِ، فَيَرَى سَبِيلَهُ، إِمَّا إِلَى الْجَنَّةِ، وَإِمَّا إِلَى النَّارِ» قِيلَ: يَا رَسُولَ اللهِ، فَالْإِبِلُ؟ قَالَ: «وَلَا صَاحِبُ إِبِلٍ لَا يُؤَدِّي مِنْهَا حَقَّهَا، وَمِنْ حَقِّهَا حَلَبُهَا يَوْمَ وِرْدِهَا، إِلَّا إِذَا كَانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ، بُطِحَ لَهَا بِقَاعٍ قَرْقَرٍ، أَوْفَرَ مَا كَانَتْ، لَا يَفْقِدُ مِنْهَا فَصِيلًا وَاحِدًا، تَطَؤُهُ بِأَخْفَافِهَا وَتَعَضُّهُ بِأَفْوَاهِهَا، كُلَّمَا مَرَّ عَلَيْهِ أُولَاهَا رُدَّ عَلَيْهِ أُخْرَاهَا، فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ، حَتَّى يُقْضَى بَيْنَ الْعِبَادِ، فَيَرَى سَبِيلَهُ إِمَّا إِلَى الْجَنَّةِ، وَإِمَّا إِلَى النَّارِ» قِيلَ: يَا رَسُولَ اللهِ، فَالْبَقَرُ وَالْغَنَمُ؟ قَالَ: «وَلَا صَاحِبُ بَقَرٍ، وَلَا غَنَمٍ، لَا يُؤَدِّي مِنْهَا حَقَّهَا، إِلَّا إِذَا كَانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ بُطِحَ لَهَا بِقَاعٍ قَرْقَرٍ، لَا يَفْقِدُ مِنْهَا شَيْئًا، لَيْسَ فِيهَا عَقْصَاءُ، وَلَا جَلْحَاءُ، وَلَا عَضْبَاءُ تَنْطَحُهُ بِقُرُونِهَا وَتَطَؤُهُ بِأَظْلَافِهَا، كُلَّمَا مَرَّ عَلَيْهِ أُولَاهَا رُدَّ عَلَيْهِ أُخْرَاهَا، فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ، حَتَّى يُقْضَى بَيْنَ الْعِبَادِ، فَيَرَى سَبِيلَهُ إِمَّا إِلَى الْجَنَّةِ، وَإِمَّا إِلَى النَّارِ» قِيلَ: يَا رَسُولَ اللهِ، فَالْخَيْلُ؟ قَالَ: «الْخَيْلُ ثَلَاثَةٌ: هِيَ لِرَجُلٍ وِزْرٌ، وَهِيَ لِرَجُلٍ سِتْرٌ، وَهِيَ لِرَجُلٍ أَجْرٌ، فَأَمَّا الَّتِي هِيَ لَهُ وِزْرٌ، فَرَجُلٌ رَبَطَهَا رِيَاءً وَفَخْرًا وَنِوَاءً عَلَى أَهْلِ الْإِسْلَامِ، فَهِيَ لَهُ وِزْرٌ، وَأَمَّا الَّتِي هِيَ لَهُ سِتْرٌ، فَرَجُلٌ رَبَطَهَا فِي سَبِيلِ اللهِ، ثُمَّ لَمْ يَنْسَ حَقَّ اللهِ فِي ظُهُورِهَا وَلَا رِقَابِهَا، فَهِيَ لَهُ سِتْرٌ وَأَمَّا الَّتِي هِيَ لَهُ أَجْرٌ، فَرَجُلٌ رَبَطَهَا فِي سَبِيلِ اللهِ لِأَهْلِ الْإِسْلَامِ، فِي مَرْجٍ وَرَوْضَةٍ، فَمَا أَكَلَتْ مِنْ ذَلِكَ الْمَرْجِ، أَوِ الرَّوْضَةِ مِنْ شَيْءٍ، إِلَّا كُتِبَ لَهُ، عَدَدَ مَا أَكَلَتْ حَسَنَاتٌ، وَكُتِبَ لَهُ، عَدَدَ أَرْوَاثِهَا وَأَبْوَالِهَا، حَسَنَاتٌ، وَلَا تَقْطَعُ طِوَلَهَا فَاسْتَنَّتْ شَرَفًا، أَوْ شَرَفَيْنِ، إِلَّا كَتَبَ اللهُ لَهُ عَدَدَ آثَارِهَا وَأَرْوَاثِهَا حَسَنَاتٍ، وَلَا مَرَّ بِهَا صَاحِبُهَا عَلَى نَهْرٍ، فَشَرِبَتْ مِنْهُ وَلَا يُرِيدُ أَنْ يَسْقِيَهَا، إِلَّا كَتَبَ اللهُ لَهُ، عَدَدَ مَا شَرِبَتْ، حَسَنَاتٍ» قِيلَ: يَا رَسُولَ اللهِ، فَالْحُمُرُ؟ قَالَ: «مَا أُنْزِلَ عَلَيَّ فِي الْحُمُرِ شَيْءٌ، إِلَّا هَذِهِ الْآيَةَ الْفَاذَّةُ الْجَامِعَةُ»: {فَمَنْ يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ، وَمَنْ يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ} [الزلزلة: 8].

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 987]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"የወርቅና የብር ባለቤት ሆኖ ሐቃቸውን የማይወጣ ሰው የትንሳኤ ቀን ለርሱ የእሳት ዝርግ ተዘርግቶለት በርሷ በጀሃነም እሳት ውስጥ ሳይቃጠል የሚቀር የለም። ጎኑም፣ ግንባሩና ጀርባውም የሚተኮስ መሆኑ አይቀርም።" በቀዘቀዘች ቁጥር እየተመላለሰች መጠኑ ሀምሳ ሺህ አመት የሚያህል ለሆነ ቀን ይተኮሳል። ይህም በባሮች መካከል ፍርድ ተፈርዶ መንገዱ ወደ ጀነት ወይስ ወደ እሳት ነው የሚለውን እስኪመለከት ድረስ የሚዘልቅ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 987]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የተለያዩ የገንዘብ አይነቶችንና የትንሳኤ ቀን ዘካቸውን ያላወጣ ሰው ምንዳ ምን እንደሆነ ገለፁ።
የመጀመሪያው: ወርቅ፣ ብርና በነርሱ ደረጃ ያለ ገንዘብና መገበያያ ሸቀጥ ነው። ይሀውም ዘካ ግዴታ ሆኖበት ያልወጣለትን ወርቅና ብር ነው። የትንሳኤ ቀን ሲሆን በዝርግ መልኩ የሚቃጠልም የሚቀልጥም ይደረጋል። በጀሃነም እሳት ውስጥም ትቀጣጠላለች በርሷም ባለቤቱ ይቀጣበታል። በርሷም ጎኑም፣ ግንባሩና ጀርባውም ይተኮሳል። በቀዘቀዘች ቁጥር ግለቷ ይመለሳል። አላህ በፍጡራን መካከል ፈርዶ ከጀነት ነዋሪዎች ወይም ከእሳት ነዋሪዎች መካከል ከአንዱ እስኪሆን የአንዱ ቀን መጠን ሀምሳ ሺህ አመት የሚያህል በሆነበት የእለተ ትንሳኤ ሙሉ ጊዜው በዚህ ሁኔታ ቅጣቱ ይቀጥላል።
ሁለተኛው: ግዴታ የሆነው ዘካዋንና ሐቋን ያልተወጣላት የግመል ባለቤት ነው። ከግመል ሐቅም እርሷ ዘንድ ለሚገኙ ድሆች በማለብ ማጠጣት ነው። ይህቺ ግመልም ተልቃ፣ ሰብታና ከነበሩበት ቁጥር በዝተው ይመጣሉ። የትንሳኤ ቀን የተስተካከለ ሰፊ መሬት ላይ ባለቤቱ ይዘረጋል፣ ይጣላል፣ ለርሷ ይለጠጣል። በእግሮቻቸውም ይረገጣል፣ በጥርሶቻቸውም ይነከሳል። የመጨረሻዋ ግመል ባለፈች ቁጥር የመጀመሪያው ይመለሳል። አላህ በፍጡራን መካከል ፈርዶ ከጀነት ነዋሪዎች ወይም ከእሳት ነዋሪዎች መካከል ከአንዱ እስኪሆን ድረስም የአንዱ ቀን መጠን ሀምሳ ሺህ አመት የሚያህል በሆነበት በእለተ ትንሳኤ ሙሉ ጊዜውን በዚህ ሁኔታ ቅጣቱ ይቀጥላል።
ሶስተኛው: ግዴታ የሆነበትን ዘካ የማያወጣለት የከብት፣ የፍየልና የበግ ባለቤት የሆነ ሰው ነው። ከነበሩበት መጠን ምንም ሳይቀነስ በዝተው ይመጣሉ። የትንሳኤ ቀን የተስተካከለ ሰፊ መሬት ላይ ባለቤቱ ተዘርግቶ ይጣላል፣ ለርሷ ይለጠጣል። ከነርሱም መካከል ቀንዱ የተጠመዘዘ፣ ቀንድ የሌለውና ቀንዱ የተሰበረ አይኖርም። ይልቁንም የተሟላ ባህሪ ተላብሰው ነው የሚመጡት። በቀንዶቻቸውም ይወጉታል፣ በእግራቸውም ይረግጡታል። የመጨረሻዋ ባለፈች ቁጥር የመጀመሪያዋ ትመለሳለች። አላህ በፍጡራን መካከል ፈርዶ ከጀነት ነዋሪዎች ወይም ከእሳት ነዋሪዎች መካከል ከአንዱ እስኪሆን ድረስ የአንዱ ቀን መጠን ሀምሳ ሺህ አመት የሚያህል በሆነበት በእለተ ትንሳኤ ሙሉ ጊዜውን በዚህ ሁኔታ ቅጣቱ ይቀጥላል።
አራተኛው: ፈረስ የሚያደልብ ነው። ይህም ሶስት አይነት ናቸው።
አንደኛ: እርሷ ለርሱ ወንጀል የሆነችበት ናት። ይህም ለይዩልኝ፣ ለፉከራና ሙስሊሞችን ለመዋጋት የያዛት እንደሆነ ነው።
ሁለተኛ: እርሷ ለርሱ የምትሸሽገው የሆነች ናት። ይህም በአላህ መንገድ ለመዋጋት የያዛት እንደሆነ ነው። ከዚያም ለፈረሷ በመቀለብ፣ ጣጣዋን በመቻል ከዚህም ውስጥ ኮርማዋን በማዘጋጀት ለርሷ መልካም የዋለ እንደሆነ ነው።
ሶስተኛ: እርሷ ለርሱ ምንዳ የምታስገኝ የሆነች ናት። ይህም በአላህ መንገድ ለሙስሊሞች ለመዋጋት የያዛትና በቡቃያ ስፍራና በጨፌ ውስጥ ያሰማራት እንደሆነ ነው። ይህቺ ፈረስ አንድም አትበላም ለርሱ በበላችው ቁጥር ምንዳ ቢፃፍለት እንጂ፤ በእበቷና ሽንቷ ቁጥር ልክ እንኳ ምንዳ ቢፃፍለት እንጂ፤ የምትታሰርበትን ገመድ ቆርጣ በምድር ከፍታ ላይ አትሮጥም አላህ ለርሱ በኮቴዋና እበቷ ቁጥር ልክ ምንዳን ቢፅፍለት እንጂ፤ ባለቤቱ እርሷን ይዞ በወንዝ በኩል ሲያልፍ እርሷን ማጠጣት ሳይፈልግም አትጠጣም አላህ በጠጣችው ቁጥር ለርሱ ምንዳ የሚፅፍለት ቢሆን እንጂ።
ቀጥሎ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለአህያ እርሷም እንደ ፈረስ አምሳያ ናትን? ተብለው ተጠየቁ።
እርሳቸውም: ከዚህች የሚያስተውላት አጭር ከሆነችው አንቀፅ በቀር እርሷን የሚመለከት አንቀፅ አልወረደም። ይህቺ አንቀፅም ሁሉንም የአምልኮና የወንጀል አይነቶችን የምታጠቃልል ናት። ይህቺም አንቀፅ {የብናኝ ክብደት ያክልም መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል። የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሰራ ሰው ያገኘዋል።} [አዝዘልዘላህ:8] የምትለዋ የአላህ ንግግር ናት። አህያን ሲያደልብ አላህ የታዘዘባት የዚህን ምንዳ ያገኛል። ወንጀል ከሰራ ደግሞ የዚህን ቅጣት ያገኛል። ይህ አንቀፅ ሁሉንም ስራዎች የሚጠቀልል ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዘካ የመስጠት ግዴታነትንና ዘካ የከለከለ ሰውም ብርቱ ዛቻ እንደተዛተበት እንረዳለን።
  2. ዘካን በስንፍና የሚከለክል ሰው ከሃዲ ባይሆንም ነገር ግን ከባድ አደጋ ውስጥ እንደሆነ እንረዳለን።
  3. የሰው ልጅ አምልኮ ሲተገብር የአምልኮውን መሰረት አስቦ ዝርዝሩን ባያስብም በሚከሰቱ ዝርዝር ነገሮች ሁሉ እንደሚመነዳ እንረዳለን።
  4. በገንዘብ ላይ ከዘካ ውጪም ሐቆች እንዳሉ እንረዳለን።
  5. ከግመል ሐቆች መካከል አንዱ የምትጠጣበት ስፍራ ባለችበት ወቅት ለሚገኙ ሚስኪኖች አልቦ ማጠጣት ነው። ይህም ፈላጊዎች ቤት ድረስ አስበው ከመምጥት ይልቅ ቀላል ስለሆነና ለግመሎቹም ምቹ ስለሆነ ነው። ኢብኑ በጧል እንዲህ ብለዋል: ገንዘብ ሁለት ሐቆች አሉት: የነፍስ ወከፍ ሐቅና ሌላ ሐቅ ነው። አልቦ ማጠጣት የመልካም ስነምግባር መገለጫ ከሆኑ ሐቆች መካከል አንዱ ነው።
  6. ከግመል፣ ከከብትና ከፍየል ግዴታ ሐቆች መካከል ኮርማዋን የፈለገች ጊዜ ኮርማዋን ማዘጋጀት ነው።
  7. የአህያና ማስረጃ ያልመጣባቸው ነገሮች ባጠቃላይ ብይን: {የብናኝ ክብደት ያክልም መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል። የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሰራ ሰው ያገኘዋል።} በሚለው የአላህ ንግግር ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።
  8. በአንቀፁ ውስጥ መልካም ስራ ትንሽ እንኳ ብትሆን በመስራት ማነሳሳትና መጥፎ ስራ ብታንስ እንኳ ከመስራት ማስጠንቀቂያ አለበት።