عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«بَيْنَمَا رَجُلٌ يَمْشِي بِطَرِيقٍ وَجَدَ غُصْنَ شَوْكٍ عَلَى الطَّرِيقِ فَأَخَّرَهُ، فَشَكَرَ اللَّهُ لَهُ فَغَفَرَ لَهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1914]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"አንድ ሰውዬ እየሄደ ሳለ መንገድ ላይ እሾካማ ቅርንጫፍ አገኘና አራቀው። አላህም ስራውን ተቀበለው። ወንጀሉንም ማረው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1914]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና‐ አንድ ሰውዬ መንገድ ላይ ሙስሊሞችን በሚያውክ በእሾካማ ዛፍ ቅርንጫፍ በኩል ሲያልፍ ቅርንጫፉን ከመንገዱ እንዳራቀውና አላህም ስራውን ተቀብሎ ወንጀሉን እንደማረው ተናገሩ።