+ -

عَنْ عُقْبَةَ بْنِ عَامِرٍ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ: قَالَ لِي رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أُنْزِلَ -أَوْ أُنْزِلَتْ- عَلَيَّ آيَاتٌ لَمْ يُرَ مِثْلُهُنَّ قَطُّ، الْمُعَوِّذَتَيْنِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 814]
المزيــد ...

ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉኝ:
"እንደነርሱ አምሳያ በጭራሽ ያልታየ አንቀጾች በኔ ላይ ወርዷል ወይም ወርደውልኛል። እነርሱም 'ሙዐወዘተይን' ናቸው።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 814]

ትንታኔ

ዑቅባ ቢን ዓሚር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ እንዲህ እንዳሉት ተናገረ: (ጥበቃን በመፈለግ በኩል) እንደነርሱ አምሳያ በጭራሽ ያልታየን አንቀጾች ዛሬ ምሽት አላህ በኔ ላይ አወረደ። እነርሱም ሙዐወዘተይን ናቸው። የ{ፈለቅ} ምዕራፍና የ{አንናስ} ምዕራፍ ናቸው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የእነዚህ ሁለት ምዕራፍ ደረጃ ትልቅነት መገለፁን እንረዳለን።
  2. በሁለቱ ምዕራፎች ከሁሉም ክፋቶች ጥበቃን በመፈለግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ሃውሳ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ተጨማሪ