عَنْ ‌أُبَيِّ بْنِ كَعْبٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«يَا أَبَا الْمُنْذِرِ، أَتَدْرِي أَيُّ آيَةٍ مِنْ كِتَابِ اللهِ مَعَكَ أَعْظَمُ؟» قَالَ: قُلْتُ: اللهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ. قَالَ: «يَا أَبَا الْمُنْذِرِ، أَتَدْرِي أَيُّ آيَةٍ مِنْ كِتَابِ اللهِ مَعَكَ أَعْظَمُ؟» قَالَ: قُلْتُ: {اللهُ لا إِلَهَ إِلا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ} [البقرة: 255]. قَالَ: فَضَرَبَ فِي صَدْرِي، وَقَالَ: «وَاللهِ لِيَهْنِكَ الْعِلْمُ، أَبَا الْمُنْذِرِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 810]
المزيــد ...

ከኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ውስጥ ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። " እርሳቸውም በድጋሚ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 810]

ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኡበይ ቢን ከዕብን የአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቁ አንቀፅ ማን ናት? በማለት ጠየቁት። መልስ ለመስጠት ካመነታ በኋላ አየቱል ኩርሲይ ናት {አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} በማለት መለሰ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በዕውቀትና ጥበብ የተሞላ መሆኑን ለመጠቆም ደረቱን በመምታት በዚህ ዕውቀት እንዲደሰትና እንዲገራለት ዱዐ በማድረግ ትክክለኛ መልስ እንደመለሰ በመጥቀስ አበረታቱት።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. የኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ትልቅ ደረጃ መገለፁ።
  2. አየቱል ኩርሲይ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቋ አንቀፅ በመሆኗ መሸምደዱ፣ ትርጉሙን ማስተንተኑና እርሱን መተግበር ተገቢ ነው።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (68)