عن أبي الدرداء رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ حَفِظَ عَشْرَ آيَاتٍ مِنْ أَوَّلِ سُورَةِ الكَهْفِ، عُصِمَ مِنَ الدَّجَّالِ». وفي رواية: «مِنْ آخِرِ سُورَةِ الكَهْف».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 809]
المزيــد ...
ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ሰው ከደጃል ይጠበቃል።" በሌላ ዘገባ "ከሱረቱል ከህፍ መጨረሻ አስር አንቀጾች… "
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 809]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን በቀልቡ የሸመደደ ሰው በመጨረሻ ዘመን መጥቶ ለራሱ ጌትነትን ከሚሞግተው ከመሲሕ ደጃል ፈተና ይጠበቃል ብለው ተናገሩ። የደጃል ፈተና አደም ከተፈጠረ ጀምሮ ትንሳኤ እስኪቆም ድረስ ምድር ከምታስተናግደው ፈተና ሁሉ ከባዱ ፈተና ነው። ተከታዮቹን ሊፈትንበት ዘንድ ከተለምዶ የወጡ አንዳንድ ተአምራት አላህ አስመችቶለታል። እነዚህን አንቀጾች መቅራት ከርሱ የሚጠብቀው ምክንያትም የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾች ውስጥ ደጃል ሰዎችን ከሚፈትናቸው ፈተናዎች የበለጠ ትላልቅ ተአምራትና አስደናቂዎች ስለሚገኙ ነው። እነዚህን አንቀጾች ያስተነተነ በደጃል አይፈተንም። በሌላ ዘገባም: "ከምዕራፉ መጨረሻ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ማለትም {እነዚያ የካዱት ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን (የማያስቆጣኝ አድርገው) አሰቡን .....} ከሚለው ጀምሮ ነው።