عن عثمان بن عفان رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ تَوَضَّأَ فَأَحْسَنَ الْوُضُوءَ خَرَجَتْ خَطَايَاهُ مِنْ جَسَدِهِ حَتَّى تَخْرُجَ مِنْ تَحْتِ أَظْفَارِهِ».

[صحيح] - [رواه مسلم]
المزيــد ...

ከዑሥማን ቢን ዐፋን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'"

Sahih/Authentic. - [Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ውዱእን ሱናዎቹና አዳቦቹን ከመጠባበቅ ጋር ያደረገ ሰው ይህ ውዱኡ ወንጀሎቹ ከእጆቹና እግሮቹ ጣቶች ስር ጭምር እስኪወጡ ድረስ ወንጀሎቹ እንዲማሩና ሀጢአቶቹ እንዲረግፉ ከሚያደርጉ ምክንያቶቹ አንዱ መሆኑን እየነገሩን ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ውዱእን ሱናዎቹንና አዳቦቹን ተምሮ በመተግበር ላይ ትኩረት እንድናደርግ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. የውዱእን ትሩፋት እንረዳለን። ውዱእ ትናንሽ ወንጀሎችን የሚያስምር ነው። ትላልቅ ወንጀሎች ግን የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።
  3. ወንጀሎች ከሰውነታችን እንዲወጡ ውዱእን ማሟላቱና ያለምንም ጉድለት ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደገለፁት መፈፀሙ መስፈርት ነው።
  4. እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ወንጀሎችን ማስማር ትላልቅ ወንጀሎችን በመራቅና ከርሱ ተውበት በማድረግ ላይ የተገደበ ነው። አላህ እንዲህ ብሏልና {ከእርሱ ከተከላችሁት ታላላቆቹን (ሀጢአቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን) ሀጢአቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን።} [አንኒሳእ:31]