عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ تَعَلَّمَ عِلْمًا مِمَّا يُبْتَغَى بِهِ وَجْهُ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ لَا يَتَعَلَّمُهُ إِلَّا لِيُصِيبَ بِهِ عَرَضًا مِنَ الدُّنْيَا لَمْ يَجِدْ عَرْفَ الْجَنَّةِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ» يَعْنِي رِيحَهَا.
[صحيح] - [رواه أبو داود وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 3664]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልዕክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፡
"የአላህ ፊት የሚፈለግበትን እውቀት የዱንያን ጥቅም ለማግኘት ካልሆነ በቀር ለሌላ ግብ የማይማረው ከሆነ የትንሳኤ ቀን የጀነትን ሽታ አያገኝም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 3664]
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመሰረቱ የአላህ ውዴታ የሚፈለግበትን ሸሪዓዊ እውቀትን የተማረ ሰው ሲማረው ግን ገንዘብን ወይም ክብርን የመሰሉ የዱንያ መጣቀሚያና ዕጣፈንታዎችን ለማግኘት ካልሆነ በቀር የማይማረው የሆነ ሰው የትንሳኤ ቀን የጀነትን ሽታ አያገኝም አሉ።