عن بريدة بن الحصيب رضي الله عنه أنه قال:
بَكِّرُوا بِصَلَاةِ الْعَصْرِ، فَإِنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: «مَنْ تَرَكَ صَلَاةَ الْعَصْرِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 553]
المزيــد ...
ከቡረይዳህ ቢን ሑሰይብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
"የዐስርን ሰላት ወቅቱ እንደገባ ቶሎ ስገዱ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋልና: ' የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 553]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዐስርን ሶላት ሆን ብሎ ወቅቱን ከማዘግየት አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመ ሰው ስራው ተበላሽቶ ከንቱ ይቀራል።