+ -

عَنْ كَعْبِ بْنِ عُجْرَةَ رضي الله عنه عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مُعَقِّبَاتٌ لَا يَخِيبُ قَائِلُهُنَّ -أَوْ فَاعِلُهُنَّ- دُبُرَ كُلِّ صَلَاةٍ مَكْتُوبَةٍ، ثَلَاثٌ وَثَلَاثُونَ تَسْبِيحَةً، وَثَلَاثٌ وَثَلَاثُونَ تَحْمِيدَةً، وَأَرْبَعٌ وَثَلَاثُونَ تَكْبِيرَةً».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 596]
المزيــد ...

ከከዕብ ቢን ዑጅራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡
"ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ አራት ጊዜ "ተክቢራ" (አላሁ አክበር) ማለት ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 596]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተናገራቸው የማይከስርበትንና የማይፀፀትበትን ዚክር ተናገሩ። እንደውም በቃላቶቹ ምንዳ የሚያገኝባቸው ናቸው። ከፊሉ ከከፊሉ በኋላ የሚባሉ ሲሆኑ ከግዴታ ሶላት በኋላ ነው የሚባሉት። እነርሱም:
"ሱብሐነላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት። ማለትም አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራት ነው።
"አልሐምዱሊላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት ነው። ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በተሟላ ምሉዕነት መግለፅ ነው።
"አላሁ አክበር"ን ሰላሳ አራት ጊዜ ማለት ነው። አላህ ከሁሉም ነገር ታላቅና የላቀ ነውና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የ"ተስቢሕ"፣ የ"ተሕሚድ"ና የ"ተክቢር"ን ትሩፋት እንረዳለን። እነርሱም ቀሪ የሆኑ መልካም ስራዎች ናቸው።