عَن أَبي مُوْسى الأَشْعريِّ رضي الله عنه قال: قال رسولُ اللهِ صلى اللهُ عليه وسلم:
«مَثَلُ الْمُؤْمِنِ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَمَثَلِ الْأُتْرُجَّةِ، رِيحُهَا طَيِّبٌ وَطَعْمُهَا طَيِّبٌ، وَمَثَلُ الْمُؤْمِنِ الَّذِي لَا يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَمَثَلِ التَّمْرَةِ، لَا رِيحَ لَهَا وَطَعْمُهَا حُلْوٌ، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ مَثَلُ الرَّيْحَانَةِ، رِيحُهَا طَيِّبٌ وَطَعْمُهَا مُرٌّ، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي لَا يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَمَثَلِ الْحَنْظَلَةِ، لَيْسَ لَهَا رِيحٌ وَطَعْمُهَا مُرٌّ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቡ ሙሳ አል-አሽዓሪይ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡
"ቁርኣንን የሚቀራ ሙእሚን ምሳሌው እንደ ትርንጎ ነው። ሽታዋም ምርጥ ነው። ጣዕሟም ምርጥ ነው። ቁርአንን የማይቀራ ሙእሚን ምሳሌው እንደ ተምር ነው። ሽታ የላትም ጣዕሟ ግን ጣፋጭ ነው። ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ ምሳሌው እንደ አሪቲ ነው። ሽታዋ ምርጥ ሲሆን ጣዕሟ ግን መራራ ነው። ቁርአንን የማይቀራ ሙናፊቅ ምሳሌው እንደ እምቧይ ነው። ሽታም የላትም ጣዕሟም መራራ ነው።'"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቁርአንን በመቅራትና በርሱ ከመጠቀም አንፃር የሰዎችን ክፍል ገለፁ።
የመጀመሪያው ክፍል: ቁርአንን የሚቀራና በርሱ የሚጠቀም ሙእሚን ሲሆን እርሱም እንደ ትርንጎ ፍሬ ምሳሌ ነው። ጣዕሙና ሽታው ምርጥ፣ መልኩ ያማረና ጥቅሙም ብዙ ነው። በሚቀራው ቁርአን ይሰራበታልም የአላህን ባሮችም ይጠቅምበታል።
ሁለተኛው: ቁርአንን የማይቀራ ሙእሚን ነው። እርሱም እንደ ቴምር ምሳሌ ነው። ጣዕሙ ምርጥ ሲሆን ሽታ ግን የለውም። ቴምር በጣዕሟ ጣፋጭነትን እንደሰበሰበችው የዚህም ሙእሚን ቀልብ ኢማንን ሰብስቧል። ቴምር ሰዎች በግልፅ የሚያሸቱት መአዛ እንደሌለው ሁሉ እርሱም ሰዎች በመስማት የሚረኩበትን አቀራር ግልፅ አያደርግም።
ሶስተኛው: ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ ነው። እርሱም እንደ አሪቲ ነው። እርሷ ምርጥ ሽታ ቢኖራትም ጣዕሟ ግን መራራ ነው። ቀልቡ በኢማን አልተስተካከለም፣ በቁርአን አይሰራም፣ ሰዎች ፊት ግን አማኝ መስሎ ይቀርባል። የርሷም ሽታ ምርጥ ነው ልክ እንደርሱ አቀራር ይመስላል። ጣዕሟ መራራ ነው ልክ እንደርሱ ክህደት ይመስላል።
አራተኛው: ቁርአን የማይቀራ ሙናፊቅ ነው። እርሱም እንደ እንቧይ ነው። ሽታ የላትምም ጣዕሟም መራር ነው። ሽታ የሌላት መሆኗ ቁርአን ስለማይቀራ ሽታ የሌለው ከመሆኑ ጋር ይመሳሰላል። ጣዕሟ መራር መሆኑ በርሱ ክህደት መራርነት ጋር ይመሳሰላል። ውስጡ ከኢማን የተራቆተ ሲሆን ውጫዊ ማንነቱም ጥቅም የሌለው እንደውም ጎጂ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ቁርአንን ሐፍዞ በርሱ የሚሰራበት ሰው ደረጃ የተገለፀ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ከማስተማሪያ መንገዶች መካከል ግንዛቤን ለማቅረብ ምሳሌ ማድረግ አንዱ ነው።
  3. አንድ ሙስሊም በአላህ መጽሐፍ ላይ ቀጣይነት ያለው ልማድ ሊኖረው እንደሚገባ እንረዳለን።