عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«تَعَاهَدُوا هَذَا الْقُرْآنَ، فَوَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لَهُوَ أَشَدُّ تَفَلُّتًا مِنَ الْإِبِلِ فِي عُقُلِهَا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 791]
المزيــد ...
ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
"ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 791]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሰው ቁርአንን በልቡ ከሸመደደው በኋላ እንዳይረሳው ቁርአንን በመጠባበቅና በማንበቡ ላይ መዘውተርን አዘዙ። ቁርአን ከልብ ውስጥ ከታሰረች ግመል የበለጠ እጅግ የሚጠፋና የሚወገድ መሆኑን ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመሀላቸው በማጠናከር ገለፁ። ግመል በክንዶቿ መሀል በገመድ ተጠፍራ ስታበቃ ሰውዬው ከተጠባበቃት ይይዛታል፤ ከለቀቃት ግን ትሄዳለችም ትጠፋለችም።