+ -

عَنِ الْبَرَاءِ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَا مِنْ مُسْلِمَيْنِ يَلْتَقِيَانِ فَيَتَصَافَحَانِ إِلَّا غُفِرَ لَهُمَا قَبْلَ أَنْ يَفْتَرِقَا».

[صحيح بمجموع طرقه] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 5212]
المزيــد ...

ከበራእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።"»

[ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 5212]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሁለት ሙስሊሞች በመንገድና መሰል ቦታ ተገናኝተው አንዱ ሌላኛውን በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተሰጣጡ ለነርሱ (ከቦታው) በአካል ወይም ከመጨባበጡ እጃቸውን ከማለያየታቸው በፊት ወንጀላቸው ይማራል ብለው ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በመገናኘት ወቅት መጨባበጥ እንደሚወደድና በዚህም ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. መናዊይ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሱና ሌላ ችግር እስከሌለ ድረስ ቀኝ እጅን ቀኝ እጅ ላይ በማሳረፍ ካልሆነ በቀር አይገኝም።»
  3. ሰላምታን በማብዛት ላይ መነሳሳቱንና አንድ ሙስሊም ሌላውን ሙስሊም ወንድሙ በመጨበጥ የሚያገኘው ምንዳ ትልቅነት መገለፁን እንረዳለን።
  4. አጅነቢይ (ባዳ የሆነችን) ሴት መጨበጥ የመሰለው ክልክል የሆነ መጨባበጥ ከዚህ ሐዲሥ ውጭ ነው።