+ -

عن ابن عباس رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«ما مِنْ أيَّامٍ العمَلُ الصَّالِحُ فيها أحبُّ إلى اللهِ مِن هذه الأيام» يعني أيامَ العشر، قالوا: يا رسُولَ الله، ولا الجهادُ في سبيلِ الله؟ قال: «ولا الجهادُ في سبيلِ الله، إلا رجلٌ خَرَجَ بنفسِه ومالِه فلم يَرْجِعْ من ذلك بشيءٍ».

[صحيح] - [رواه البخاري وأبو داود، واللفظ له] - [سنن أبي داود: 2438]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:
'ከነዚህ ቀናቶች የበለጠ መልካም ስራዎች ወደ አላህ ተወዳጅ የሚሆኑበት ምንም ቀን የለም።' ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ናቸው። ሰሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአላህ መንገድ ጂሃድ ማድረግም ቢሆን?' በማለት ጠየቁ። እሳቸውም 'በአላህ መንገድ ጂሃድም ቢሆን እንኳ (አይበልጥም) ነፍሱና ገንዘቡን ይዞ የወጣና ከነዚህ መካከል አንዱም ያልተመለሰለት ሙጃሂድ ሲቀር' አሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና፣አቡዳውድ ሲዘግቡት የዚህ ዘገባ ቃልም የአቡዳውድ ዘገባ ነው።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2438]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዙልሒጃ ወር የመጀመሪያ አስር ቀናቶች ውስጥ መልካም ስራዎችን መስራት በአመቱ ውስጥ ከሚገኙ ቀናቶች ሁሉ የበለጠ መሆኑን ገለፁ።
ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከነዚህ አስር ቀናት ውጪ ጂሃድ ማድረግ? ወይስ ከጂሃድ ውጪ ያሉ መልካም ስራዎችን በነዚህ ቀናት ውስጥ መስራት? የትኛው እንደሚበልጥ ጠየቁ። ይህም እነርሱ ዘንድ ጂሃድ ከሁሉም በላጭ ስራ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዳይ ስለሆነ ነው።
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም በነዚህ ቀናቶች መልካም ስራዎችን መስራት ከነዚህ ውጭ ባሉት ቀናት ከሚደረግ ጂሃድም ይሁን ሌሎች ስራዎች የበለጠ እንደሆነ ተናገሩ። ይህ ግን በአላህ መንገድ ገንዘቡንና ነፍሱን አጋልጦ ሙጃሂድ ሆኖ የወጣና በአላህ መንገድ ገንዘቡንም ያጣ ነፍሱንም የሰዋ ሲቀር ነው። በነዚህ ከፍ ባሉት ቀናቶች የሚሰሩ ስራዎችን የሚበልጠው ይህ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوكرانية الجورجية المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የዙልሒጃ አስሩ ቀናት መልካም ስራዎች ትሩፋትን እንረዳለን። ሙስሊም የሆነ ሰው እነዚህ ቀናትን አላህን በማውሳት፣ ቁርአን በመቅራት፣ በተክቢር፣ በተሕሊል፣ በተሕሚድ፣ ሶላት በመስገድ፣ በሶደቃ፣ በፆምና በሁሉም በጎ ስራዎች ሊሸምትበትና አምልኮን ሊያበዛበት ይገባል።