+ -

عَنْ عُثْمَانَ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«مَا مِنَ امْرِئٍ مُسْلِمٍ تَحْضُرُهُ صَلَاةٌ مَكْتُوبَةٌ فَيُحْسِنُ وُضُوءَهَا وَخُشُوعَهَا وَرُكُوعَهَا، إِلَّا كَانَتْ كَفَّارَةً لِمَا قَبْلَهَا مِنَ الذُّنُوبِ، مَا لَمْ يُؤْتِ كَبِيرَةً، وَذَلِكَ الدَّهْرَ كُلَّهُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 228]
المزيــد ...

ከዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ:
'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው እንጂ፤ ይህም እድሜልኩን ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 228]

ትንታኔ

አንድም ሙስሊም የግዴታ ሶላት ወቅት የሚገባበትና ዉዱኡን አሳምሮና አሟልቶ የሚያደርግ፤ ቀጥሎም ቀልቡና አካሉ ሁሉ ወደ አላህ የዞሩና የአላህን ልቅና ያስተዋሉ በሚሆኑበት መልኩ በሶላቱ የሚመሰጥ፤ እንደ ሩኩዕ፣ ሱጁድና ሌሎችንም የመሳሰሉትን የሶላቱን ድርጊቶች የሚያሟላ አይሆንም ይህ ሶላቱ ላሳለፈው ትናንሽ ወንጀሎች ማስማሪያ ቢሆን እንጂ፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል የሆነን አንድም ወንጀል እስካልሰራ ነው። ይህ ትሩፋትም ዘመናት በነጎዱ ቁጥር በሁሉም ሶላቶች ላይ እንደሚቀጥል ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገለፁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የባሪያውን ወንጀል የሚያስምረው ሶላት ዉዱኡን ያሳመረበትና የአላህን ፊት በመፈለግ በተመስጦ የሰገደው ሶላት ነው።
  2. በአምልኮ ላይ የመዘውተር ትሩፋትን እንረዳለን። አምልኮ ትናንሽ ወንጀሎችን የሚያስምር አንዱ ሰበብ ነው።
  3. ዉዱእን የማሳመር፣ ሶላትን የማሳመርና በሶላት ውስጥ የመመሰጥን ትሩፋት እንረዳለን።
  4. ትናንሽ ወንጀሎች እንዲማሩ ትላልቅ ወንጀሎችን መራቅ ወሳኝ እንደሆነ እንረዳለን።
  5. ትላልቅ ወንጀሎች በተውበት ካልሆነ በቀር አይማሩም።
ተጨማሪ