+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلَّى الله عليه وسلم قال:
«ما مِنْ أحَدٍ يُسلِّمُ علي إلا ردَّ اللهُ عليَّ رُوحي حتى أردَّ عليه السَّلامَ».

[إسناده حسن] - [رواه أبو داود وأحمد] - [سنن أبي داود: 2041]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አንድም በኔ ላይ ሰላምታን የሚያቀርብ የለም ለርሱ ሰላምታን እስክመልስ ድረስ አላህ ለኔ ነፍሴን የሚመልስልኝ ቢሆን እንጂ።"

[ሰነዱ ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2041]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከቅርብም ይሁን ከሩቅ ሆኖ በርሳቸው ላይ ሰላምታን ባቀረበ ሁሉ ላይ ሰላምታን ሊመልሱ ዘንድ ነፍሳቸው እንደምትመለስላቸው ተናገሩ። የቀብርና የበርዘኽ ህይወት የሩቅ ጉዳይ ነው። ከአላህ በቀርም እውነታውን የሚያውቅ የለም። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶላትና ሰላም በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በቀብር ውስጥ የሚያሳልፉት ህይወት የሰው ልጅ በበርዘኽ ከሚያሳልፈው ህይወት ባጠቃላይ የተሟላው ህይወት ነው። ተጨባጭ እውነታውንም ከአላህ በቀር ማንም አያውቀውም።
  3. ይህ ሐዲሥ የሽርክ ባለቤቶች በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እርዳታ ለመጠየቅ ማስረጃ እስከማድረግ በሚያበቃቸው ልክ ለጥጠው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እኛ እንደምንኖረው አይነት ህይወት አላቸው ለሚል ሰው ማስረጃነት የለውም። ይህ ህይወት የበርዘኽ ህይወት ነውና።