عَنِ الأَسْوَدِ بنِ يَزِيدَ قَالَ:
سَأَلْتُ عَائِشَةَ مَا كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَصْنَعُ فِي بَيْتِهِ؟ قَالَتْ: كَانَ يَكُونُ فِي مِهْنَةِ أَهْلِهِ -تَعْنِي خِدْمَةَ أَهْلِهِ-، فَإِذَا حَضَرَتِ الصَّلاَةُ خَرَجَ إِلَى الصَّلاَةِ.
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 676]
المزيــد ...
ከአስወድ ቢን የዚድ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«ዓኢሻን ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቤት ውስጥ ስለሚሰሩት ስራ ጠየቅኳት? እርሷም: "የሚያሳልፉት ቤተሰባቸውን በማገልገል ነው። ሶላት ሲደርስ ሶላት ለመስገድ ይወጣሉ።" አለች።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 676]
የአማኞች እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቤታቸው ውስጥ ስለነበራቸው ሁኔታ ተጠየቁ። ጊዜያቸውን እንዴት ነበር ያሳልፉ ይሰሩ የነበሩት? እርሷም: እንደማንኛውም ሰው እርሳቸውም ሰው ነበሩ። ወንዶች ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩትን ይሰሩ ነበር። ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ያገለግሉ ነበር። ፍየላቸውን ያልባሉ፣ ልብሳቸውን ይሰፋሉ፣ ጫማቸውን ይጠግናሉ፣ የተቀደደ ባልዲያቸውን ይለጥፋሉ። ሶላት ኢቃም የሚልበት ወቅት ላይ ሲደርሱ ምንም ሳያዘገዩ ወደርሷ ይወጣሉ በማለት መለሰች።