+ -

عَنِ أبي زُهير عُمَارَةَ بْنِ رُؤَيْبَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم:
«لَنْ يَلِجَ النَّارَ أَحَدٌ صَلَّى قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ غُرُوبِهَا»

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 634]
المزيــد ...

ከአቡ ዙሀይር ዑማረህ ቢን ሩአይበህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ፀሐይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 634]

ትንታኔ

የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የፈጅርን ሶላትና የዐስርን ሶላት የሰገደና በመስገድም የዘወተረ አንድም ሰው (የጀሀነም) እሳት እንደማይገባ ተናገሩ። እነዚህን ሁለት ሶላቶች የለዩት ከባባድ ሶላቶች ስለሆኑ ነው። የሱብሒ ወቅት በጣፋጭ እንቅልፍ ወቅት የሚሰገድ ነው፤ የዐስር ወቅት ደግሞ ሰው በቀን ስራና ንግድ በሚጠመድበት ጊዜ የሚሰገድ ነው። ይህ አይነት ችግር ከመኖሩም ጋር እነዚህን ሁለት ሶላቶች የተጠባበቀ ሰው በተቀሩትም ሶላቶች ላይ መጠባበቁ አይቀርም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሱብሒና የዐስር ሶላቶችን ደረጃና በነርሱ ላይ መጠባበቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
  2. እነዚህን ሶላቶች የሚያከናውነው አብዛኛው ሰው ነፍሱ ከስንፍናና ይዩልኝ ያገለለች ሆና አምልኮም የሚወድ ይሆናል።
ተጨማሪ