عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«لَأَنْ أَقُولَ: سُبْحَانَ اللهِ، وَالْحَمْدُ لِلهِ، وَلَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَاللهُ أَكْبَرُ، أَحَبُّ إِلَيَّ مِمَّا طَلَعَتْ عَلَيْهِ الشَّمْسُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2695]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል: "የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፡
''ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ ወላኢላሃ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር' ማለቴ ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ (ከሚሰጠኝ) የበለጠ ወደእኔ እጅግ ተወዳጅ ነው።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2695]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ትላልቅ ቃላቶች አላህን ማወደስ ከዱንያና በውስጧ ካለው ሁሉ የተሻለ መሆኑን ተናገሩ። እነሱም:
"ሱብሓነሏህ" ይህም አላህን ከጉድለት ማጥራት ነው።
"አልሐምዱሊላህ" ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕ ባህሪያቶቹ ማወደስ ነው።
"ላኢላሃ ኢለሏህ" ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም።
"አሏሁ አክበር" አላህ ከሁሉም ነገር የበለጠ ታላቅ ነው ማለት ነው።