عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيَّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ -وَكَانَ غَزَا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ثِنْتَيْ عَشْرَةَ غَزْوَةً- قَالَ: سَمِعْتُ أَرْبَعًا مِنَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَأَعْجَبْنَنِي، قَالَ:
«لاَ تُسَافِرِ المَرْأَةُ مَسِيرَةَ يَوْمَيْنِ إِلَّا وَمَعَهَا زَوْجُهَا أَوْ ذُو مَحْرَمٍ، وَلاَ صَوْمَ فِي يَوْمَيْنِ: الفِطْرِ وَالأَضْحَى، وَلاَ صَلاَةَ بَعْدَ الصُّبْحِ حَتَّى تَطْلُعَ الشَّمْسُ، وَلاَ بَعْدَ العَصْرِ حَتَّى تَغْرُبَ، وَلاَ تُشَدُّ الرِّحَالُ إِلَّا إِلَى ثَلاَثَةِ مَسَاجِدَ: مَسْجِدِ الحَرَامِ، وَمَسْجِدِ الأَقْصَى، وَمَسْجِدِي هَذَا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1995]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው ‐ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር አስራ ሁለት ዘመቻዎችን ዘምቷል። ‐ እንዲህ አለ: "አራት ነገሮችን ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰምቼ አስደንቀውኛል። እንዲህ ብለዋል:
'ሴት ልጅ ከርሷ ጋር ባሏ ወይም ዘመዷ ከሌሉ በቀር ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድን አትጓዝ። ሁለት ቀናት ላይ መፆም የለም፤ ዒደል ፊጥርና አድሓ። ከሱብሒ በኋላ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ሶላት የለም፤ ከዐስር በኋላም ፀሀይ እስክትገባ ድረስም ሶላት የለም። ወደ ሶስት መስጂዶች ካልሆነ በቀርም ጓዝን ሸክፎ አይኬድም: ወደ መስጂደል ሐራም፣ ወደ መስጂደል አቅሷና ወደዚህ መስጂዴ።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1995]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአራት ጉዳዮች ከለከሉ።
የመጀመሪያው: ሴት ልጅን ያለባሏ ወይም ያለ አንድ ዘመዷ ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድ ከመጓዝ መከልከል ነው። ዘመዷ የተባሉትም እንደ ልጅ፣ አባት፣ የወንድም ልጅ፣ የእህት ልጅ፣ አጎትና የመሳሰሉት ያሉ ለዘላለም በነርሱ ላይ ለጋብቻ እርም የተደረገችባቸው ቅርብ ዘመዶቿ ናቸው።
ሁለተኛው: የዒደል ፊጥርና የዒደል አድሓ ቀንን የመፆም ክልክልነት ነው። በነዚህ ቀናቶች ላይ አንድ ሙስሊም ለስለትም ወይም ለበጎ ፍቃደኝነትም ወይም ለማካካሻ ብሎም መፆሙ ክልክል ነው።
ሶስተኛው: ከዐስር ሶላት በኋላ ፀሀይ እስክትገባ ድረስና ጎህ ከቀደደ በኋላ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ሱና ሶላትን ከመስገድ መከልከሉ ነው።
አራተኛው: ከነዚህ ሶስት መስጂዶች በቀር ወደ ማንኛውም ስፍራ ወደርሱ የመጓዝን ብልጫ አስቦ፣ በመጓዝ ምክንያትም ምንዳ ይነባበራል ብሎ በማመን መጓዝ መከልከላቸው ነው። ከነዚህ ሶስት መስጂዶች በቀርም በውስጧ ለመስገድ በሚል ጓዝ ተሸክፎ አይኬድም። ከነዚህ ሶስት መስጊዶች በቀርም ምንዳ አይነባበርምና። እነሱም: መስጂደል ሐራም፣ የነቢዩ መስጂድና መስጂደል አቅሷ ናቸው።