عَنْ عُقْبَةَ بْنَ عَامِرٍ الْجُهَنِيَّ رضي الله عنه قَالَ:
ثَلَاثُ سَاعَاتٍ كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَنْهَانَا أَنْ نُصَلِّيَ فِيهِنَّ، أَوْ أَنْ نَقْبُرَ فِيهِنَّ مَوْتَانَا: حِينَ تَطْلُعُ الشَّمْسُ بَازِغَةً حَتَّى تَرْتَفِعَ، وَحِينَ يَقُومُ قَائِمُ الظَّهِيرَةِ حَتَّى تَمِيلَ الشَّمْسُ، وَحِينَ تَضَيَّفُ الشَّمْسُ لِلْغُرُوبِ حَتَّى تَغْرُبَ.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 831]
المزيــد ...
ከዑቅባህ ቢን ዓሚር አልጁሀኒይ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
"የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሶስት ወቅቶች ላይ ከመስገድ ወይም ሟቾቻችንን ከመቅበር ይከለክሉን ነበር። ፀሃይ በምትወጣ ጊዜ ከፍ እስክትል ድረስ፤ ፀሐይ እኩኩል (መሃል አናት ላይ) በምትሆን ወቅት የሚቆም ሰው (ያለ ምንም ጥላ) የሚቆም ከሆነበት ወቅት ፀሐይ ወደ መግቢያዋ እስክትዘነበል ድረስ፤ ፀሃይ ለመግባት በምትዘነበልበት (በምትቀርብበት) ወቅት እስክትገባ ድረስ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 831]
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከቀኑ ክፍለ ጊዜ በሶስት ወቅቶች ላይ ሱና ሶላቶችን ከመስገድ ወይም ሟቾችን ከመቅበር ከለከሉ: የመጀመሪያው ወቅት: ፀሃይ በምትወጣ ጊዜ ነው። ይህም ገና መጀመሪያ ስትወጣ ነው። ክልከላውም የጦር ርዝመት ያህል ከፍ እስክትል ድረስ ነው። ቆይታውም እስከ ሩብ ሰአት አካባቢ ይገመታል። ሁለተኛው: ፀሐይ በሰማዩ መሃል ላይ በምትሆንበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅትም በምስራቅም ሆነ በምዕራብ አቅጣጫ ጥላ አይኖራትም። ክልከላውም ከሰማዩ መሃል ወደ ምዕራብ ዘንበል እስክትል ድረስ ነው። በዚህም ጊዜ ጥላ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ዘንበል ማለት ይጀምራል። ይህም የዙህር ሶላት ወቅት የሚጀምርበት ወቅት ነው። ይህ የክልከላው ወቅትም አጭር ጊዜ ነው። አምስት ደቂቃ አካባቢ ይገመታል። ሶስተኛው: ፀሐይ ለመግባት በምትዘነበልበትና በምትጀምርበት ወቅት ነው። ክልከላውም እስክትገባ ድረስ ነው።