عَن زَيْدِ بْنِ خَالِدٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ جَهَّزَ غَازِيًا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَقَدْ غَزَا، وَمَنْ خَلَفَ غَازِيًا فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِخَيْرٍ فَقَدْ غَزَا».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2843]
المزيــد ...
ከዘይድ ቢን ኻሊድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በአላህ መንገድ የሚዘምትን ያሰናዳ ሰው በርግጥም ዘምቷል። በአላህ መንገድ ለዘመተ ሰው (ቤተሰብ) በመልካም ትብብሩ የተተካ በርግጥም ዘምቷል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2843]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ለሚዘምት ሰው መሳሪያ፣ መጓጓዣ፣ ምግብ፣ ቀለብና ሌሎችም ለጉዞው የግድ የሚያስፈልገውን ነገር ያሰናዳ ሰው ልክ እንደዘማቹ እንደሚቆጠርና የዘማቾቹን ምንዳ እርሱም እንደሚያገኝ ተናገሩ።
የዘማችን ጉዳይ በመልካም ሊሸፍን ሃላፊነት የወሰደ ሰውና እርሱ (ዘማቹ) በራቀበት ወቅት ቤተሰቦቹን ሊንከባከብ የርሱን ቦታ የተተካ ሰውም ልክ እንደዘማች እንደሚቆጠር ተናገሩ።