+ -

عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا عَدْوَى، وَلَا طِيَرَةَ، وَيُعْجِبُنِي الْفَأْلُ» قَالَ قِيلَ: وَمَا الْفَأْلُ؟ قَالَ: «الْكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2224]
المزيــد ...

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በራሱ የሚተላለፍ ተላላፊ በሽታ የለም፣ ገድም የለም ተስፈኝነት (በጎ ምኞት) ግን ያስደስተኛል።" "አልፈእል (በጎ ምኞት) ምንድነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "መልካም ንግግር ነው።" አሉ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2224]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሽታ ከአንዱ ወደ ሌላው ያለ አላህ ውሳኔ በራሱ ይተላለፋል የሚለው የድንቁርና ዘመን ሰዎች ያምኑት የነበረው እምነት የተሳሳተ ከንቱ እምነት መሆኑን ተናገሩ። የገድ እምነትም ከንቱ አጉል እምነት ነው። እርሱም በማንኛውም የሚሰማ ወይም የሚታይ ወፍ ወይም እንስሳ ወይም አካል ጉዳተኞችን ወይም ቁጥሮች ወይም ቀናት ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች ላይ ተመርኩዞ ገደቢስነትን ማመን ነው። ወፍን ያወሱት በድንቁርና ዘመን የታወቀው ገድ ማለት በርሱ ስለነበር ነው። መሰረቱም ስራ ወይም ጉዞ ወይም ንግድ ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ጉዳይ ሊጀምሩ ሲፈልጉ ወፍን ይለቃል። ወፊቱ ወደ ቀኝ ከበረረች ጥሩ ገድ በማመን ወደፈለገው ይጓዛል። ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረች ደግሞ ገደቢስነትን በማመን ከፈለገው ጉዳይ ይቆጠባል። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "አልፈእል" (በጎ ምኞት) እንደሚያስደስታቸው ተናገሩ። እርሱም የሰው ልጅ ከሰማው መልካም ቃል አንፃር የሚያጋጥመው የደስታና ሀሴት ስሜት ነው። ይህም በጌታው ላይ መልካም እሳቤ እንዲኖረው ያደርጋልና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከአላህ በቀር መልካምን የሚያመጣና ከአላህ በቀርም መጥፎን የሚከላከል ስለሌለ በአላህ ላይ መመካት እንደሚገባ እንረዳለን።
  2. የገድ እምነት መከልከሉን እንረዳለን። እርሱም ሰው ገድ የሚልበትና ከስራ የሚያቅበው ነገር ነው።
  3. "አልፈእል" ከተከለከለው የገድ እምነት መካከል አይደለም። ይልቁንም ያ በአላህ ላይ መልካም እሳቤ ማሳደር ነው።
  4. ሁሉም ነገር በብቸኛውና አጋር በሌለው በአላህ ውሳኔ ነው የሚከሰተው።
ተጨማሪ