عن عمرو بن شُعيب عن أبيه عن جدِّه قال: قال رسولُ الله صلى الله عليه وسلم:
«مُرُوا أولادكمِ بالصلاةِ وهم أبناءُ سبعِ سِنينَ، واضرِبوهم عليها وهم أبناءُ عَشرٍ، وفرِّقوا بينهم في المَضاجِعِ».

[حسن] - [رواه أبو داود]
المزيــد ...

ዐምር ቢን ሹዐይብ ከአባቱና ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!"

Sahih/Authentic. - [At-Tirmidhi]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አባት ወንድና ሴት ልጆቹን ገና ሰባት ዓመት እያሉ ሶላት እንዲሰግዱ ማዘዝና ሶላትን በማስተካከል ላይ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ማስተማር እንዳለበት ገለፁ። አስር ዓመት የደረሱ ጊዜም ትእዛዙን ይጨምራል። ሶላትን በማጓደላቸው ይመታቸዋልም፤ በመኝታ ስፍራም በመካከላቸውም ይለያያቸዋል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ህፃናት ልጆችን አቅመ አዳም ከመድረሳቸውም በፊት የዲን ጉዳዮችን ማስተማር እንደሚገባ እንረዳለን። ከአንገብጋቢዎቹ መካከልም አንዱ ሶላት ነው።
  2. መምታቱ ለሥርዓት (ለማስተማር) እንጂ ለመቅጣት አይደለምና ሁኔታውን በሚመጥን መልኩ መቅጣት ይገባል።
  3. ሸሪዓ ክብርን ለመጠበቅ የሰጠውን ትኩረትና ወደ ብክለት የሚያደርስን መንገድ ሁሉ መዝጋቱን እንረዳለን።