+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنينَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا قَالَتْ:
مَا صَلَّى النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ صَلاَةً بَعْدَ أَنْ نَزَلَتْ عَلَيْهِ: {إِذَا جَاءَ نَصْرُ اللَّهِ وَالفَتْحُ} [النصر: 1] إِلَّا يَقُولُ فِيهَا: «سُبْحَانَكَ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي». وعَنْها قَالَتْ: كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُكْثِرُ أَنْ يَقُولَ فِي رُكُوعِهِ وَسُجُودِهِ: «سُبْحَانَكَ اللهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللهُمَّ اغْفِرْ لِي» يَتَأَوَّلُ الْقُرْآنَ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4967]
المزيــد ...

ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ" ይሉ ነበር።» ትርጉሙም "ጌታችን ሆይ! ከምስጋና ጋር ጥራት የተገባህ ነህ! አላህ ሆይ! ማረኝ።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4967]

ትንታኔ

የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተናገረችው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} የሚለው ምዕራፍ የወረደላቸው ጊዜ ቁርአኑን ወደ ተግባር ለመለወጥ {ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው! ምህረትንም ለምነው።} የሚለውን የአላህን ትእዛዝ ፈጥነው ለመፈፀም በሶላት መሀል በሩኩዓቸውና በሱጁዳቸው ወቅት እንዲህ ማለትን ያበዙ ነበር፡ "ሱብሓነከ" ለአንተ ከማይመጥን ከሁሉም ጉድለት አንተን አጠራኸለሁ። "አልላሁምመ ረበና ወቢሐምዲክ" ዛትህ፣ ባህሪህና ድርጊትህ ምሉዕ ስለሆነ ምስጉን በሆኑ ውዳሴዎች አወድስሃለሁ። "አልላሁምመግፊርሊ" ከኔ ላይ ወንጀሌን አብስ! ይቅር በለኝ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በሩኩዕና በሱጁድ ወቅት ይህን ዱዓ ማብዛት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. በእድሜ መጨረሻ ወቅት ምህረት መጠየቅ እንደሚገባ እንረዳለን። ልክ እንደዚሁ አምልኮ ውስጥ የተከሰቱ ጉድለቶች እንዲሟሉም አምልኮዎችን (በተለይም ሶላትን) ምህረትን በመጠየቅ እንድናጠናቅቅ ያስገነዝባል።
  3. ዱዓ ተቀባይነት እንዲያገኝ ወደ አላህ ከምንቃረብባቸው ነገሮች መካከል ያማረው መመስገኛዎቹን ማውሳትና እርሱን ከጉድለቶችና ነውሮች የጠራና የፀዳ መሆኑን ማውሳት ነው።
  4. አላህን ምህረት መጠየቅ ያለው ትሩፋትና በሁሉም ሁኔታዎች ተፈላጊ መሆኑን እንረዳለን።
  5. የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አምልኮ የተሟላ መሆኑንና የአላህንም ትእዛዝ በተሟላ መልኩ መተግበራቸውን እንረዳለን።
ተጨማሪ