+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَدْعُو وَيَقُولُ: «اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ عَذَابِ القَبْرِ، وَمِنْ عَذَابِ النَّارِ، وَمِنْ فِتْنَةِ المَحْيَا وَالمَمَاتِ، وَمِنْ فِتْنَةِ المَسِيحِ الدَّجَّالِ». وفِي لَفْظٍ لِمُسْلِمٍ: «إِذَا فَرَغَ أَحَدُكُمْ مِنَ التَّشَهُّدِ الْآخِرِ، فَلْيَتَعَوَّذْ بِاللهِ مِنْ أَرْبَعٍ: مِنْ عَذَابِ جَهَنَّمَ، وَمِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ، وَمِنْ فِتْنَةِ الْمَحْيَا وَالْمَمَاتِ، وَمِنْ شَرِّ الْمَسِيحِ الدَّجَّالِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1377]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና): 'አሏሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወሚን ዓዛቢ‐ን‐ናር ወሚን ፊትነቲል መሕያ ወል መማት ወሚን ፊትነቲል መሲሒ‐ድ‐ደጃል' 'ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።' እያሉ ዱዓእ ያደርጉ ነበር።" በሙስሊም ዘገባ 'አንዳችሁ ከመጨረሻው ተሸሁድ ያጠናቀቀ ጊዜ ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቅ: ከጀሀነም ቅጣት፣ ከቀብር ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተናና ከመሲሕ ደጃል ክፋት።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1377]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ከሶላት ከማሰላመታቸው በፊት ከአራት ነገሮች በአላህ ይጠበቁ ነበር። እኛንም በአላህ ከነርሱ እንድንጠበቅ አዘዙን።
የመጀመሪያው: ከቀብር ቅጣት ነው።
ሁለተኛው: የትንሳኤ ቀን ከእሳት ቅጣት ነው።
ሶስተኛው: ከህይወት ፈተናዎች ሲባል ክልክል ከሆኑ ዓለማዊ ዝንባሌዎችና አጥማሚ ማደናገሪያዎች፤ እንዲሁም በሞት ሰአት ከሚያጋጥሙ ፈተናዎች ሲባል ደግሞ በጣእረ ሞት ሰአት ከኢስላም ወይም ሱና መጥመምን የመሰሉ ወይም በሁለቱ መላእክት መጠየቅን ከመሰለ የቀብር ፈተና ማለት ነው።
አራተኛ: በመጨረሻ ዘመን የሚወጣ ከሆነው ከመሲሕ ደጃል ፈተና ነው። አላህ በርሱ አማካኝነት ባሮቹን ይፈትናል። ዱዓው ላይ እርሱ ተለይቶ የተጠቀሰው የርሱ ፈተናና ማጥመሙ ከባድ ስለሆነ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. እነዚህ መጠበቂያ ዱዓዎች ከዱንያና ከመጨረሻው ዓለም ክፋቶች መጠበቅን ከሰበሰቡ አንገብጋቢና ጠቅላይ ከሆኑ ዱዓዎች መካከል ናቸው።
  2. የቀብር ቅጣት የተረጋገጠና እውነት መሆኑን እንረዳለን።
  3. የፈተናን አደገኝነት እና ከፈተና ለመዳን በአላህ መታገዝና ዱዓ ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. የደጃል መውጣት የተረጋገጠ መሆኑንና ፈተናው ከባድ መሆኑን እንረዳለን።
  5. ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ይህን ዱዓ ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  6. ከመልካም ስራ በኋላ ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
ተጨማሪ