عن ثَوْبَانَ رضي الله عنه قال:
كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا انْصَرَفَ مِنْ صَلَاتِهِ اسْتَغْفَرَ ثَلَاثًا، وَقَالَ: «اللَّهُمَّ أَنْتَ السَّلَامُ، وَمِنْكَ السَّلَامُ، تَبَارَكْتَ ذَا الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ»، قَالَ الْوَلِيدُ: فَقُلْتُ لِلْأَوْزَاعِيِّ: كَيْفَ الْاسْتِغْفَارُ؟ قَالَ: تَقُولُ: أَسْتَغْفِرُ اللهَ، أَسْتَغْفِرُ اللهَ.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 591]
المزيــد ...
ከሠውባን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ (ምህረት ይጠይቁ) ነበር። እንዲህም ይሉ ነበር: 'አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም' (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) ወሊድ ለአውዛዒይ 'እንዴት ነው ኢስቲግፋር የሚደረገው? አልኩት' አለ። እሳቸውም 'አሰተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ' በማለት ነው ብለው መለሱልኝ።' አለ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 591]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ "አስተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ" ይሉ ነበር።
ቀጥለውም ጌታቸውን "አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም" (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) በማለት ጌታቸውን ያልቃሉ። አላህ በባህሪያቶቹ የተሟላና ሰላም ነው፤ ከሁሉም ጉድለትና ነውርም የጠራ ነው። ከዱንያና አኺራ ክፋት ሰላም የሚፈለገውም ከሌላ ሳይሆን ከርሱ ነው። እርሱ ጥራት ይገባውና በሁለቱም ዓለም መልካሙ የበዛ ፣ የልቅናና መልካም ባለቤት ነው።