+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ سَبَّحَ اللهَ فِي دُبُرِ كُلِّ صَلَاةٍ ثَلَاثًا وَثَلَاثِينَ، وَحَمِدَ اللهَ ثَلَاثًا وَثَلَاثِينَ، وَكَبَّرَ اللهَ ثَلَاثًا وَثَلَاثِينَ، فَتْلِكَ تِسْعَةٌ وَتِسْعُونَ، وَقَالَ: تَمَامَ الْمِائَةِ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ غُفِرَتْ خَطَايَاهُ وَإِنْ كَانَتْ مِثْلَ زَبَدِ الْبَحْرِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 597]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
«ከሁሉም (ግዴታ) ሶላት በኋላ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያጠራ (ሱብሓነሏህ) ያለ፤ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያመሰገነ (አልሐምዱ ሊላህ) ያለ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ተክቢራ (አላሁ አክበር) ያለ፤ ይህም በድምሩ ዘጠና ዘጠኝ ሲሆን መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ወንጀሉ የባህር አረፋ አምሳያ ቢደርስ እንኳ ይማራል።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 597]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላቶች ከተጠናቀቁ በኋላ እነዚህን ያለ ሰው የሚያገኘውን ምንዳ ገለፁ:
ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ሱብሓነላህ": ይህም አላህን ከጉድለቶች ሁሉ ማጥራት ነው።
ሰላሳ ሶስት ጊዜ "አልሐምዱ ሊላህ": ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕ ባህሪያቱ ማወደስ ነው።
ሰላሳ ሶስት ጊዜ "አላሁ አክበር": ማለት ይህም አላህ ከሁሉም ነገር እጅግ የላቀ ነው ማለት ነው።
መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ‐ ትርጉሙም፦ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የለውም። ጥራት የተገባው አላህ በምሉዕ ንግስና የተለየና ከርሱ ውጪ ያሉት የማይገባቸውን ከውዴታና ልቅና ጋር ውዳሴና ሙገሳ የተገባው ነው። እርሱም ምንም የማይሳነው ቻይ ነው። ‐
እነዚህን ቃላት ያለ ሰው ወንጀሉ ባህር በሚናወጥና በሚላተም ሰአት ከላይ በሚሆነው ነጭ አረፋ ልክ ቢበዛ ራሱ ትማራለችም ትሰረዛለችም።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከግዴታ ሶላቶች በኋላ ይህን ዚክር ማለት ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
  2. ይህ ዚክር ለወንጀል መማር ምክንያት ነው።
  3. የአላህን ትልቁን ችሮታ፣ እዝነትና ምህረት እንረዳለን።
  4. ይህ ዚክር ወንጀሎችን ለማስማር ምክንያት ነው። የተፈለገውም: ትናንሽ ወንጀሎችን ማስማር ነው፤ ትላልቅ ወንጀሎች ግን ከተውበት በቀር ምንም አያስምራቸውም።
ተጨማሪ