+ -

عَنِ ابْنَ مَسْعُودٍ رضي الله عنه قَالَ:
عَلَّمَنِي رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، وَكَفِّي بَيْنَ كَفَّيْهِ، التَّشَهُّدَ، كَمَا يُعَلِّمُنِي السُّورَةَ مِنَ القُرْآنِ: «التَّحِيَّاتُ لِلَّهِ، وَالصَّلَوَاتُ وَالطَّيِّبَاتُ، السَّلاَمُ عَلَيْكَ أَيُّهَا النَّبِيُّ وَرَحْمَةُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ، السَّلاَمُ عَلَيْنَا وَعَلَى عِبَادِ اللَّهِ الصَّالِحِينَ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ». وفي لفظ لهما: «إِنَّ اللهَ هُوَ السَّلَامُ، فَإِذَا قَعَدَ أَحَدُكُمْ فِي الصَّلَاةِ فَلْيَقُلْ: التَّحِيَّاتُ لِلَّهِ وَالصَّلَوَاتُ وَالطَّيِّبَاتُ السَّلَامُ عَلَيْكَ أَيُّهَا النَّبِيُّ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ، السَّلَامُ عَلَيْنَا وَعَلَى عِبَادِ اللهِ الصَّالِحِينَ، فَإِذَا قَالَهَا أَصَابَتْ كُلَّ عَبْدٍ لِلَّهِ صَالِحٍ فِي السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ، أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ، ثُمَّ يَتَخَيَّرُ مِنَ الْمَسْأَلَةِ مَا شَاءَ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6265]
المزيــد ...

ከኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄ በእጃቸው መካከል ሆኖ አንድን የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሩኝ ተሸሁድን አስተማሩኝ። 'አትተሒይያቱ ሊላሂ ወስሶለዋቱ ወጥጦይዪባቱ አስ‐ሰላሙ ዐለይከ አይዩሃን-ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ፤ አስ‐ሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አስ‐ሷሊሒን፤ አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ትርጉሙም: “ክብርና ልዕልና እንዲሁም ሶላቶችና መልካም ነገሮች ሁሉ ለአላህ ናቸው፡፡ አንቱ ነቢዩ ሆይ! የአላህ ሰላም፣ እዝነቱና በረከቶች በእርሶ ላይ ይስፈን ፤ ሰላም በእኛና በአላህ ደጋግ ባሮችም ላይ ይስፈን፤ ከአላህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሐመድም የአላህ አገልጋይና መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡”።)" በሌላ የቡኻሪና ሙስሊም ዘገባ "አላህ እርሱ ሰላም ነው። አንዳችሁ ሶላት ላይ በተቀመጠ ወቅት 'አትተሒይያቱ ሊላሂ ወስሶለዋቱ ወጥጦይዪባቱ አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሃን-ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ፤ አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን' ይበል። ይህንን ያለ ጊዜ በሰማይም ውስጥ ሆነ በምድር ውስጥ የሚገኝ ደግ የአላህ ባሪያ ሁሉ ዱዓው ይደርሰዋል። ቀጥሎ 'አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' ይበል ከዚያም የፈለገውን ዱዓእ መርጦ ያድርግ!"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6265]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና አንድ የቁርኣን ምእራፍ እንደሚያስተምሩት ትኩረቱ ወደርሳቸው ለመሰብሰብ እጁን በእጃቸው ውስጥ አድርገው ሶላት ውስጥ የሚባለውን ተሸሁድ አስተማሩት። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለተሸሁድ በቃል ደረጃም ይሁን በመልዕክት ደረጃ የሰጡትን ትኩረት የሚጠቁም ነው። እንዲህም አሉ: "አትተሒይያቱ ሊላህ… " ይህ ማለት: ክብርና ልቅናን የሚጠቁም ንግግርም ይሁን ተግባር ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው ማለት ነው። "… አስሶለዋቱ… " ይህም ማለት የታወቁት ግዴታ ሶላቶችም ይሁኑ ሱና ሶላቶች ለአላህ ናቸው ነው። "… አጥጦይዪባቱ… " ይህም ማለት: ምሉዕነትን የሚጠቁሙ ጥሩ ንግግሮች፣ ተግባሮችና ባህሪያቶች ሁሉ ለአላህ የተገቡ ናቸው ማለት ነው። "… አስሰላሙ ዐለይከ አይዩሀን-ነቢዩ ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ… " "አንቱ ነቢይ ሆይ! ሰላም፣ የአላህ እዝነትና በረከቱ በርሶ ላይ ይሁን" ይህም ለርሳቸው ከሁሉም መከራና ጉዳት ሰላም እንዲሆኑና ሁሉም መልካም ነገሮች እንዲጨምርላቸውና እንዲበዛላቸው የምናደርገው ዱዓእ ነው። "… አስሰላሙ ዐለይና ወዓላ ዒባዲልላሂ አስሷሊሒን… " (በአላህ ደጋግ ባሮችና በኛ ላይም ሰላም ይስፈን።) ይህም በሰማይ ውስጥም ሆነ በምድር ውስጥ ለሚገኝ ደግ ባሪያና ለሰጋጁ ሁሉ ሰላም እንዲሰፍንበት የሚደረግ ዱዓእ ነው። … አሽሀዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ… " "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ እመሰክራለሁ።" ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ቁርጥ የሆነ ማረጋገጥን አረጋግጣለሁ ማለት ነው። "… ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ" "ሙሐመድ የአላህ ባሪያና መልክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።" ማለትም: ለርሳቸው በባርነትና በመጨረሻ መልዕክተኛነት አረጋግጣለሁ።
ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰጋጁ የፈለገውን ዱዓእ እንዲመርጥ አነሳሱ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በሁሉም ሶላት ውስጥ የዚህ ተሸሁድ ስፍራው ከመጨረሻው ሱጁድ በኋላ በምንቀመጥበት ወቅት እና ባለ ሶስትና አራት ረከዓ ሶላት ከሆነ ደግሞ ከሁለተኛው ረከዓ በኋላም ነው።
  2. በተሸሁድ ወቅት "አትተሒያቱ" ግዴታ መሆኑን እንረዳለን። ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከተረጋገጡ የተሸሁድ ቃላቶች መካከል በማንኛውም ቢጠቀም ይበቃለታል።
  3. ሶላት ውስጥ በወንጀል እስካልሆነ ድረስ በማንኛውም ደስ ባለው ዱዓእ ማድረግ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
  4. ዱዓ ላይ ከነፍስ መጀመር እንደሚወደድ እንረዳለን።
ተጨማሪ