عن ابنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما عن النبيِّ صلى الله عليه وسلم قال:
«أُمِرْتُ أَنْ أَسْجُدَ عَلَى سَبْعَةِ أَعْظُمٍ: عَلَى الْجَبْهَةِ وَأَشَارَ بِيَدِهِ عَلَى أَنْفِهِ، وَالْيَدَيْنِ، وَالرُّكْبَتَيْنِ، وَأَطْرَافِ الْقَدَمَيْنِ، وَلَا نَكْفِتَ الثِّيَابَ وَالشَّعَرَ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በሰባት አጥንቶቼ ሱጁድ እንዳደርግ ታዝዣለሁ። በግንባሬ በማለት በእጃቸው ወደ አፍንጫቸው አመላከቱ፣ በሁለቱ እጆቼ፣ በሁለቱ ጉልበቴ፣ በሁለቱ እግር ጣቶቼ ፤ ልብሳችንንም ይሁን (ለወንዶች) ፀጉራችንን እንዳንሰበስብም ታዘናል።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ላይ በሰባት አካላቶች ሱጁድ እንዲወርዱ አላህ ያዘዛቸው መሆኑን ገለፁ።
የመጀመሪያው: ግንባር ነው። እርሱም: ከአፍንጫና ሁለት አይኖች በላይ ያለው የተዘረጋ የፊት ክፍል ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግንባርና አፍንጫ ከሰባቱ አካላት እንደ አንድ አካል መሆናቸውን ለመግለፅና ሱጁድ አድራጊ በአፍንጫው መሬት መንካት እንዳለበት ለመግለፅ በእጃቸው ወደ አፍንጫቸው ጠቆሙ።
ሁለተኛውና ሶስተኛው አካል: ሁለት እጆች ናቸው።
አራተኛውና አምስተኛው: ሁለቱ ጉልበቶች ናቸው።
ስድስተኛውና ሰባተኛው: የሁለት እግሮች ጣቶች ናቸው።
ወደ መሬት ሱጁድ በምናደርግበት ወቅት መሬቱን እንዳይነካ ለመጠበቅ ብለን ፀጉራችንን ከመጠቅለል ወይም ልብሶቻችንን ከመሰብሰብ ከለከሉን። በተቃራኒው መሬት ላይ እንዲያርፍና ከሰውነታችን ጋር አብሮ ሱጁድ እንዲወርድ መልቀቅ እንዳለብን አዘዙን።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሶላት ላይ በሰባት አካላት ሱጁድ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ልብስንና ፀጉርን ሶላት ውስጥ መሰብሰብና መጠቅለል እንደሚጠላ እንረዳለን።
  3. አንድ ሰጋጅ ሶላት ውስጥ የመረጋጋት ግዴታ አለበት። ይህም ሰባቱን የሱጁድ አካላት መሬት ላይ በማሳረፍና የተደነገገውን ውዳሴ እስኪፈፅም ድረስ እዛው ላይ በመርጋት ነው።
  4. ፀጉርን የመጠቅለል ክልከላው በወንዶች ላይ ብቻ የተገደበ ነው። ሴት ልጅ ሶላት ውስጥ እንድትሸፋፈን (እንድትሰተር) የታዘዘች ናትና።
ተጨማሪ