عَنْ أَنَسٍ رَضيَ اللهُ عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَتَبَاهَى النَّاسُ فِي الْمَسَاجِدِ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والنسائي وابن ماجه] - [سنن أبي داود: 449]
المزيــد ...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች በመስጂድ ጉዳይ ሳይፎካከሩ ሰዓቲቱ አትቆምም።"
[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 449]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከትንሳኤ ቀን መቅረብና የዱንያ መጠናቀቅ ምልክቶች መካከል አንዱ ሰዎች መስጂዶችን በማስዋብ መፎካከራቸው ነው። ወይም አላህን ከማውሳት ውጪ ለሌላ አላማ ባልተገነቡ መስጂዶች ውስጥም በዱንያቸው መፎካከራቸው ነው።